ነሐሴ 5 ፣ 2013

በኦሎምፒክ ድሎቻቸዉ ምንጊዜም የሚታወሱ ሶስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች

City: Addis Ababaስፖርት

ኢትዮጵያ ምንም እንኳን ለመጀመሪያ ጊዜ የሜልቦርን ኦሎምፒክ ዉድድር ላይ ምንም አይነት ሜዳሊያ ማግኝት ያልቻለች ቢሆንም በ1960 እ.ኤ.አ በሮም ኦሎምፒክ በአበበ ቢቂላ አማካኝነት የመጀመሪያዉን የወርቅ የሜዳሊያ ማስመዝገብ ችላለች።

በኦሎምፒክ ድሎቻቸዉ ምንጊዜም የሚታወሱ ሶስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ ዉድድር ላይ የተሳተፈችው እ.ኤ.አ በ1956 የሜልቦርን ኦሎምፒከ ሲሆን በውድድሩ ምንም አይነት ሜዳሊያ ማግኝት አልቻለችም ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባሉት ቀጣይ ዉድድሮች ዉስጥ በተለያዩ አትሌቲክስ ዘርፎች በተለይ በመካከለኛና በረጅም ርቀት ሩጫዎች ተሳትፎዋን ቀጥላለች፡፡ ኢትዮጲያ በኦሎምፒክ የመጀመሪያዉን የወርቅ የሜዳሊያ ያገኘችዉ በእ.ኤ.አ በ1960 በሮም ኦሎምፒክ አበበ ቢቂላ በማራቶን ባስመዘገበዉ አስደናቂ ድል ነበር፡፡

የዘንድሮዉን ጨምሮ በኦሎምፒክ ታሪክ ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 23 የወርቅ ፣ 11 የብር እና 21 ነሀስ  በድምሩ 53 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡

በአንድ የኦሎምፒክ ላይ በተለያዩ ዉድድሮች በመሳተፍ ከአንድ በላይ ሜዳሊያዎችን ማግኘት እጂግ ፈታኝ መሆኑ ይነገራል፡፡ ለዚህ ድል የበቁ አትሌቶችም ትልቅ ክብርና አድናቆት ሲቸራቸዉ ይታያል፡፡ ከኢትዮጵያዊያን አትሌቶች መካከል በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማግኝት የቻሉ ሶስት ድንቅ አትሌቶችን አጭር ታሪክና በዉድድሮቹ ያሳዩትን ብቃት እናካፍላችሁ፡፡

ምሩጽ ይፍጠር

ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ኢትዮጵያ ውስጥ ገናና ስም ካላቸው አትሌቶች ከነአበበ በቂላ፣ ማሞ ወልዴ፣ ኃይሌ ገ/ሥላሴና ከመሳሰሉት አንዱ ነው:: ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር በትግራይ ክልል በአጋሜ አውራጃ በአዲግራት ወረዳ ቱርክሶ በሚባል ቦታ ተወለደ።

ምሩፅ ከታወቅባቸው ርቀቶች ዋናዎቹ የአስርና የአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ሩጫዎች ሲሆኑ በ1972 በሞስኮ ኦሎምፒክ ሻምበል ምሩፅ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ሜትሮች ዉድድር የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማግኘት የቻለ ድነቅ አትሌት ነዉ፡፡

በሞስኮ ኦሎምፒክ በእነዚህ ርቀቶች የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ በመሆን በአለማቀፍ ደረጃ አድናቆትን ካተረፉ አትሌቶች መካከል አንዱ ለመሆን በቅቷል። ከዚህ በተጨማሪም ምሩፅ በ1964 እ.ኤ.አ.በሙኒክ ኦሎምፒክ በ10 ሺ ሜትር ለሃገሩ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ምሩጽ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክስ

በዚሁ ወቅት ባሳየዉ የተለየ የአጨራረስ ብቃት «ማርሽ ለዋጩ» የሚል ቅፅል ስፖርቱን ይዘግቡ በነበሩ ጋዜጠኞች ተሰጥቶታል። የሻምበል ምሩፅ የሩጫ ስልትና አጨራረስ በተተኪ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ለማሳደር አንደቻለም ይነገራል፡፡

ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ በተደጋጋሚ በሰጣቸው ቃለ መጠይቆች እንደገለፀው ወደሩጫ አለም በገባ ጊዜ አንደአርአያ ይመለከታቸው ከነበሩ ስፖርተኞች አንዱና ዋናው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ነበር፡፡  

የኦሎምፒክ ጀግናው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር በሳምባ ጽኑ በሽታ በስደት በሚኖርበት ካናዳ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ72 ዓመታቸው ታኅሣሥ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ምሩጽ ይፍጠር የ3 ልጆች አባት የነበሩ።

ጥሩነሽ ዲባባ

በአንድ የኦሎምፒክ ዉድድር ላይ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኝት ከኢትዮጲያዊያን ሴት አትሌቶች ዉስጥ በብቸኝነት የምትጠቀሰዉ ጥሩነሽ ዲባባ በአስደናቂ የአጨራረስ ብቃቷ በርካታ አድናቆቶችን ማትረፍ ችላለች፡፡

ጥሩነሽ እ.ኤ.አ. በ2008 በቤጂንግ በተደረገዉ ኦሎምፒክ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትሮች ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማግኘት ስትችል በዚሁ ዉድድር በ10ሺህ ሜትር ውድድር በ 29:54.66 በመግባት የአዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን በቅታለች። የክብረ ወሰኑም ባለቤት የነበረችው የጥሩነሽ ዲባብ አክስት ደራርቱ ቱሉ ነበረች። 

ጥሩነሽ ዲባባ በ2012 በለንደን ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ካሸነፈች በኋላ

ጥሩነሽ ዲባባ በተሳተፈችባቸዉ አጠቃላይ የኦሎምፒኮች 3 የወርቅ እና 3 የነሀስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከኢትዮጲያ የመጀመሪያዋ አትሌት ለመሆን ችላለች፡፡ ከኦሎምፒክ ባለፈ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ጨምሮ በርካታ አለማ አቀፍ ዉድድሮችን ላይ በመሳተፍ በርካታ ድሎችን ያስመዘገበች አትሌት ናት፡፡

ጥሩነሽ በአለም አቀፍ ደረጃ አመቱ ታላቅ አትሌት የሚሉ በርካታ ሽልማቶችን ማግኘት የቻለች ሲሆን፡፡ አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንም አስደናቂ የሴት አትሌት በማለት ሽልማት አበርክቶላታል። ተመሳሳይ ሽልማት በ 2005 ቀደም ብሎ ተበርክቶላታል።

ቀነኒሳ በቀለ

ታላቁ የረጅም ርቀት ሯጭ ቀነኒሳ በቀለ በ5ሺ እና 10ሺ ሜትር የተለያዩ አለም አቀፍ እና የኦሎምፒክ ክብረ ወሰኖች ባለቤት የሆነ ታዋቂ አትሌት ነው::  ቀነኒሳ ቤጂንግ በኦሎምፒክ  በ5 እና 10 ሺ ሜትሮች የወርቅ ሜልያዎችን የወሰደ ሲሆን በዚህ ምክኒያት ስማቸዉ ከሚጠቀሱ ኢትዮጲያዊያኝ አትሌቶች አንዱ ነዉ፡፡

ቀነኒሳ በቀለ በ 2016 የሪዮ ኦሎምፒክ ካሸነፈ በኋላ

አትሌት ቀነኒሳ በአቴንስ ኦሎምፒክ በ5ሺ ሜትር፣ በአለም ሻምፕዮንም በተለያየ ጊዜ የወርቅ ሜዲያሊያዎችን ማግኘት የቻለ አትሌት ነዉ:: የሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴን ፈለግ እንደተከተለ የሚነገርለት ቀነኒሳ ለረጅም ጊዜ የሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴን ይዞት የቆየውን ክብረ ወሰን በማሻሻሉ “ቀነኒሳ አንበሳ” የሚል ዘፈን በታዋቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የተዘፈነለት ታላቅ አትሌት ነው:: 

ቀነኒሳ በቀለ በኦሎምፒክ ዉድድር በአጠቃላይ 3 የወርቅ እና 1 የብር በድምሩ አራት የኦሎምፒክ ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአለም ሻምፒዮና እና ሌሎች አለም አቀፍ ዉድድሮችን በድል ማጠናነቅ የቻለ ድንቅ ኢትዮጲያዊ አትሌት ነዉ፡፡

አስተያየት