ነሐሴ 5 ፣ 2013

ስለኮሜርስ ሕንጻ መፍረስ መረጃ እንደሌለው የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ

City: Addis Ababaአካባቢማህበራዊ ጉዳዮችወቅታዊ ጉዳዮች

ከጣሊያን ወረራ በኋላ በ1935 ዓ.ም. የተቋቋመው የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት (ኮሜርስ) በ15 ቀናት ውስጥ እንዲፈርስ ስለመወሰኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

ስለኮሜርስ ሕንጻ መፍረስ መረጃ እንደሌለው የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ

ከ100 በላይ መምህራን፣ ከ200 በላይ ሰራተኞች፣ ከ5ሺህ በላይ ተማሪዎች ያሉት፣ ከጣሊያን ወረራ በኋላ በ1935 ዓ.ም. የተቋቋመው የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት (ኮሜርስ) በ15 ቀናት ውስጥ እንዲፈርስ ስለመወሰኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስር የሚተዳደረው ኮሌዱ በተቻኮለ ሁኔታ እንዲፈርስ የተወሰነው የሚገኝበት አካባቢ የፋይናንሻል ማዕከል ተብሎ የተለየ በመሆኑ እንደሆነ የትምህርት ቤቱ ዲን ዶ/ር ወርቁ መኮንን ለአዲስ ዘይቤ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ጉዳዩ በደብዳቤ ባይደርሳቸውም የትምህርት ተቋማት ወደሚገኙበት አራት ኪሎ አካባቢ እንዲዘዋወር መወሰኑን እንደሰሙ ነግረውናል፡፡

የፋይናንስ ተቋማትን ለሚመሩ እና የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ በርካታ ተማሪዎችን ያፈራው ትምህርት ቤቱ በቅርስነት የተመዘገበ በመሆኑ ሊፈርስ ነው የሚለው ዜና ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮም የኮሜርስ ኮሌጅ ሕንጻ ይፈርሳል ስለመባሉ የደረሰኝ ሕጋዊ መረጃ የለኝም ብሏል፡፡ ቢሮው በ2013 ዓ.ም. ባካሄደው የቅርሶች ምዝገባ እና ክለሳ ከመዘገባቸው 316 ቅርሶች መካከል የኮሜርስ ሕንጻ አንዱ መሆኑን ለመገናኛ ብዙኃን የተናገሩት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ዳይሬክተሩ አቶ ደረጄ ሥዩም ናቸው፡፡

ስለጉዳዩ ቢሯቸው በሕጋዊ መንገድ የደረሰው ደብዳቤም ሆነ መረጃ ስላለመኖሩ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተናገሩት ኃላፊው ቅርሱን በተመለከተ የሚካሄዱ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች ቢሮው ማወቅ አለበት ብለዋል፡፡

ቱሪዝም ቢሮው ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ለቂርቆስ ክ/ከ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሥፍራው በቅርስነት የተመዘገበ ስለመሆኑ ያሳወቀ ሲሆን፤ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት በግልባጭ አሳውቋል፡፡

አስተያየት