መጋቢት 10 ፣ 2013

ሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ አከፋፋይ በማጣት ምርት ተከማቸብኝ አለ

ወቅታዊ ጉዳዮች

ሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ያመረተውን ዘይት ወደ ተጠቃሚ የሚያደርስለ ጅምላ ነጋዴ ማጣቱን ተናገረ፡፡

Avatar: Lidiya Fikru
ሊዲያ ፍቅሩ

Lidiya Firkru is a mobile journalist from Dire Dawa city at Addis Zeybe

ሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ አከፋፋይ በማጣት ምርት ተከማቸብኝ አለ

በድሬዳዋ ኢንዱሰትሪ መንደር የሚገኘው “ሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ” ያመረተውን ዘይት ወደ ተጠቃሚ የሚያደርስለ ጅምላ ነጋዴ ማጣቱን ተናገረ፡፡ አከፋፋዮች ባለመቅረባቸው ምክንያት 3 ሚልዮን ሊትር ዘይት መጋዘን ተከማችቶ ይገኛል፡፡ የሀገሪቱን አጠቃላይ የዘይት ፍላጎት በአንድ ሦስተኛ ለማሟላት የሚያስችለው አቅም ላይ የሚገኘው ድርጅቱ ንግድ ሚንስትር ባወጣው የዋጋ ተመን መሰረት ለማከፋፈል ዝግጅቱን ቢያጠናቅቅም ፍላጎት ያላቸው ነጋዴዎች አልቀረቡም፡፡

‹‹የሕብረተሰቡን የዘይት ፍላጎት ለማርካት የማስፋፊያ ግንባታዎችን አከናውኖ በቀን 130 ቶን ከማምረት ወደ 950 ቶን ዘይት የማምረት አቅም ላይ ደርሷል›› የሚሉት የሸሙ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሚካኤል ጉዑሽ በወር ሦሰት ሚልዮን ሊትር እያመረተ እንደሚገኝ እንደነገሯት የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር ከድሬዳዋ ዘግባለች፡፡

‹‹በሚንስትር መሥሪያቤቱ የተፈቀደላቸውን አከፋፋዮች እየጠበቅን ነው›› የሚሉት ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋሚካኤል የመንግሥት አካላት ተመርቶ የተቀመጠውን ዘይት ለማኅበረሰቡ በማዳረስ ገበያውን እንዲያረጋጉ አሳስበዋል፡፡

ከድሬዳዋ ከተማ ወጣ ብሎ በድሬዳዋ ኢንዱሰትሪ መንደር የሚገኘው ሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በ2010 ዓ.ም. ሥራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

አስተያየት