መጋቢት 9 ፣ 2014

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት የቀብር ስነ-ስርአት በነገው ዕለት ይፈጸማል ተባለ

City: Gonderዜና

የኢንጅነር ስመኘው አባት የአባ በቀለ ዓይናለም የቀብር ስነ-ስርአት ነገ መጋቢት 10 ይፈጸማል ተባለ።

Avatar: Getahun Asnake
ጌታሁን አስናቀ

ጌታሁን አስናቀ በጎንደር የሚገኝ የአዲስ ዘይቤ ዘጋቢ ነው።

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት የቀብር ስነ-ስርአት በነገው ዕለት ይፈጸማል ተባለ
Camera Icon

ፎቶ፡ ጌታሁን አስናቀ

የኢንጅነር ስመኘው አባት የአባ በቀለ ዓይናለም የቀብር ስነ-ስርአት ነገ መጋቢት 10 ይፈጸማል ተባለ። አባ በቀለ ባደረባቸው ህመም ሆስፒታል ገብተው ከወጡ በኋላ በቤታቸው የተለያዩ መድኃኒቶች በመውሰድ ላይ የነበሩ ሲሆን ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጥዋቱ 4፡30 አካባቢ በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። 

የቀብር ስነ-ስርአታቸው "ሳቢያ ሳይና" ቀበሌ በልዩ ስሙ "ሸንበቂት" በተባለው አካባቢ በምትገኘው የቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ቀድሞ በተዘጋጀ የመቃብር ስፍራ ነገ ማለዳ የቀብር ስነ-ስርአታቸው እንደሚፈጸም ይጠበቃል። 

በቤታቸው ተገኝቶ የቀብር ስነ-ስርአቱን በማስተባበር ላይ የሚገኘው የቅርብ ዘመድ አቶ ሰለሞን መንግስቴ “የሞታቸው ዜና በስፋት አልተሰማም። ለቅርብ ዘመዶች ስልክ ደውለን እየተናገርን ነው” ሲል ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል፡፡

ለበርካታ ዓመታት የህዳሴው ግድብ ሥራ አስኪያጅ በመሆን ያገለገሉት ኢንጅነር ስመኘው አባት አባ በቀለ በቀድሞው አውራ ጎዳና መስሪያ ቤት ለረዥም ዘመናት አገልግለዋል።

አስተያየት