በደበቡ አፍሪካ በተደረሰው የፕሪቶሪያው ስምምነትን ተከትሎ መቋጫውን ያገኘው የሰሜኑ ጦርነት በትግራይ ነዋሪዎች የዕለት ከዕለት ኑሮ ላይ ለውጥ ማሳየት መጀመሩ አዲስ ዘይቤ ከስፍራው ያገኘችው መርጃ ያመላክታል።
ባለፉት 2 ዓመታት በነበረው አስከፊ ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት አቋርጠው የነበሩ አገልግሎት ሰጭዎች ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ስራ ጀምረዋል።
በጦርነቱ ወቅት ለአንድ ሊትር ነዳጅ ከ600 ብር በላይ እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ምክንያት ለ15 ዓመታት በትራንስርቱ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው 5 ቤተሰብ ሲያስታድሩ የነበሩት አቶ አብረሃ ግደይ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት በመጀገራቸው ስራ አቁመው እንደነበር ይገልጻሉ።
“በጦርነቱ ምክንያት ለአንድ ጀሪካ ነዳጅ እስከ 11000 ብር እንድንከፍል እንገደድ ነበር፡፡ በዚሁ ምክንያት መኪናዬን ቤት አቁሜ በእግሬ እጓዝ ነበር” የሚሉት አቶ አብርሃ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ በፌደራል መንግስቱና በትግራይ ክልል አስተዳደሮች መካከል በተደረገው መግባባት በተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም ወደ ቀደመ ስራቸው ተመልሰዋል።
የሰላም እጦት በትራንስፖርቱ ዘርፍ ላይ ያስከተለውን ጫና ሲገልጹ “አብዛኛው ትግራዊ እንኳን በመኪና ይቅርና በእግር መጓጓዝም ብርቅ ሆኖበት” እንደነበር በማስታወስ የታየውን አንጻራዊ ሳላም ተከትሎ ህዝቡ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን መጀመሩ እንዳስደሰታቸውም አቶ አብርሃ ይገልጻሉ።
“ህዝቡ በተጀመረው የትራንስርት አገልግሎት በዘላቂነት ተጠቃሚ መሆን እንዲችል የተጀመረው የነዳጅ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ ሊቀርብ ይገባል” የሚሉት አቶ አብርሃም የአቅርቦት እጥረት እንዳይከስ ስጋታቸውን ያጋራሉ።
“ጦርነት በመኪና ቀርቶ በእግር እንኳን ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ሁኔታን እንደሚፈጥር” በራሴ ደርሶ አይቻለው የሚሉት አቶ አብርሃ “በትራንስርት አገልግሎት ዘርፍ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ተሰማርተው አምስት የቤተሰብ አባላትን እያስተዳደሩ ሳለ በሰላም እጦት ሳቢያ በተፈጠረው የነዳጅ እጥረት ምክንያት መኪናቸውን አቁመው ስራ በመፍታታቸው ለችግር መጋለጣቸውን” ያስታውሳሉ።