የጥላቻ ንግግር ዐውድ በኢትዮጵያ
ሰዎች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው የተለያዩ መልዕክቶችን ሲለዋወጡ የሚያስፈልጋቸውን መረጃዎችሲያገኙ ኖረዋል። ይህም ያላቸውን የእርስ በርስ መስተጋብር፣ ስልተ ምርታቸውን እና የአኗኗር ዘይቤይወስናል። በዘመናት ርቀት ውስጥ የቋንቋዎች ልዩነት፣ የቦታ ርቀት እና መልዕክቶቻቸውን የሚገልጹበትመንገድ መለያየት ሳያግዳቸው አወንታዊም ሆነ አሉታዊ አሻራውን ባሳረፈ የተግባቦት ሂደት ውስጥአልፈዋል።
ባለፉት አስር ዓመታት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ መከሰት ደግሞ ለማሰብ በሚከብድ መልኩ የሰው ልጆችንየመልዕክት እና የሀሳብ ልውውጥ አዲስ ቅርጽ እንዲይዝ አድርጎታል። በዋናነት የመረጃ ማግኛ ምንጭየነበሩትን እንደ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በመገዳደር ኢንተርኔት የሰውልጆችን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ሆኗል። በተለይ እያንዳንዱን ተጠቃሚ ግለሰብ ከግዙፍ የሚዲያ ተቋማትእኩል ወሬ ነጋሪ ያደረጉት ማኀበራዊ ሚዲያዎች ብዙ በረከቶችን ይዘው የቢሊዮኖችን ቀልብ ስበውእየተስፋፉ ይገኛሉ።
ከዚህ በተቃራኒው ማህበራዊ ሚዲያው የተለያዩ ስጋቶችንም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። በዋናነት ተጠቃሽከሆኑት ስጋቶች መካከልም የጥላቻ ንግግር አንዱ ነው። በዚህም ግለሰቦችና ቡድኖች ማህበራዊ ሚዲያውንበመጠቀም የጥላቻ ንግግሮችን በምስል፣ በጽሑፍ፣ በድምጽና የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ያሰራጫሉ።ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩ የጸረ ጥላቻ አመለካከቶችም በፍጥነት በአንድ ጊዜ በዓለም ዙሪያለሚገኙ ተጠቃሚዎች ይዳረሳሉ። ከዚህ ባህሪው በመነሳትም በተለያየ መልኩ የሚንጸባርቁ የጥላቻንግግሮችን በቀላሉ ለመቆጣጠር አዳጋች አድርጎታል።
በአንጻሩ የጥላቻ ንግግር በዚህ ዘመን ተከሰተ በዚህ ዘመን ደግሞ አበበ ለማለት የሚያበቃ ተጨባጭ ማስረጃባይኖርም ማህበራዊ ሚዲያ ከመምጣቱ በፊትም የነበረ መሆኑን የሀገራችንም ሆነ የዓለም ታሪክ ያስረዳል።በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአውሮፓ በጀርመን የነበረው የፀረ-ሴማዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ከሩብምዕተ ዓመት በፊት በሩዋንዳ የደረሰው ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት በታሪክ ተጠቃሽ ከሆኑት ውስጥ ዋነኞቹናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በመላው አውሮፓስደተኞችን ማዕከል ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮችየፖለቲካውን አውድ እስከመቀየር ደርሰዋል። እንዲሁም ዘርን መሰረት በማድረግ የነጭ የበላይነትንየሚሰብኩ ቡድኖችም ከማህበራዊ ሚዲያው እገዳ ተጥሎባቸዋል። በተጨማሪም የማይናማር ወታደራዊኃላፊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በሮሂንጊዎች ላይ የዘር ማጥፋት አድርሰዋል በሚል ዓለምአቀፍ ውግዘት እንደደረሰባቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
የጥላቻ ንግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችልወይንም እንዲህ ነው ብሎ ለመተርጎምየሚያበቃአንድ ወጥ ትርጉም እንዳልተቀመጠለትምባለሙያዎቹ ይናገራሉ።ሆኖምየጥላቻ ንግግር ሐሳብንበነጻነት ከመግለጽናከእኩልነትመብትጋር ጠንካራ ግንኙነት አለው። የጥላቻ ንግግርም እንዲህ ነው ብሎለመናገር በመጀመሪያ እነዚህ ሁለት መብቶች ያላቸውን ግንኙነትእና ልዩነትማስቀመጥ ወደ ነጥቡ ለመድረስ እንደመንደርደሪያ ያገለግለናል።
ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትእናአመለካከትን የመያዝመብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ ከሚደረግላቸውመሰረታዊ መብቶች መካከል ዋነኛው ነው። በውስጡ ከሚያካትታቸው ጉዳዮች መካከልምማንኛውም ሰውበውስጡ ያለውን የፈለገውን ነገር እንዲገልጽእንዲሁምመረጃዎችን ወይንም ማንኛውንም ሀሳብየመጠየቅ፣ የመቀበል እና የማስተላለፍመብቶችን ያካትታል።ከዚህ ባለፈም ሀሳብን በነጻነት መግለጽሌሎችን ሊያስከፉ የሚችሉ አመለካከቶችን እስከ ማራመድመድረስ እንዳለበት የሚከራከሩም አልጠፉም።
በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችምሀገራት ለእነዚህ መብቶች ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባቸውምይነሳል።በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ9 ንዑስ ቁጥር4 ላይ ኢትዮጵያ ያጸደቃቻቸው ዓለም አቀፍስምምነቶች የሀገሪቱ ሕግ አካል እንደሆኑም ይደነግጋል።
በዚህ መሰረትም አንቀጽ29 ላይማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነፃነትእንዳለው በመጥቀስይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንምዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችንእንደሚያካትት ይደነግጋል።
ሆኖም ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ገደብ ሊጣልባቸው ከሚችሉ ድንጋጌዎች መካካል አንዱ ነው።በኢፌዴሪ ህገ መንግሥትም የወጣቶችን ደኀንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊገደቦች በእነዚህ መብቶች ላይ ሊደነገጉ እንደሚችሉ እና የጦርነት ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርንየሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በሕግ ገደብ እንደሚጣልባቸው ይጠቅሳል።
የጥላቻ ንግግር ለማየት ስንነሳ በሁለተኛ ደረጃ ማየት የሚገባን ጉዳይ ደግሞ የእኩልነት መብትን ነው።የእኩልነት መብት ማንኛውም ሰው የሰብዓዊ መብቱ ተከብሮያለምንም አድሎ በእኩልነት የመታየትመብትን ይደነግጋል። እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌም በአንቀጽ7 ላይ ሁሉም ሰዎችበህግ ፊት እኩል ናቸው ሁሉም ሰዎች ያለምንም ልዩነት እኩል የሆነ ህጋዊ ከለላ እና ጥበቃ የማግኘትመብት እንዳላቸው ያነሳል።
ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገው የኢፌዴሪ ህገመንግስትም አንቀጽ25 ላይ ስለእኩለልነትመብት የሚያነሳ ሲሆንሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነትሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በዚህ ረገድ በዘር፣ በብሔር፣ ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በፆታ፣በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኀበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያትልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።
እንግዲህ የጥላቻ ንግግር ለማየት ሁለት መሰረታዊ የሚባሉ ሐሳብን ወይንም አመለካከትን በነጻነትየመግለጽ እና የእኩልነት መብትን ከዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና ከኢፌዴሪ ህገመንግስት አንጻር በጥቂቱአይተናል። አሁን ደግሞ በጥቅሉ አንድ ንግግር የጥላቻ ንግግር የሚያሰኘው ምንድነው የሚለውን እናያለን።
ከላይ ለመዳሰስ እንደሞከርነው የጥላቻ ንግግር በዋናነት የተቀመጠ አንድ ወጥ ትርጉም ባይኖረውምመሰረታዊ የሚባሉ መግባባቶች እንዳሉት ግን ይታመናል። ተጠቃሽ ከሆኑት መካከልም በዓለም አቀፍ ደረጃየዘር መድሎን መሰረት በማድረግ የጸረ ጥላቻ ድንጋጌ በእ.ኤ.አ1965 መውጣቱ ይታወሳል። ድንጋጌውምአራት ነገሮችን ለይቶ አስቀምጧል። እነርሱም የዘር የበላይነትን እና የዘር ጥላቻ ላይ የሚያተኩሩ ሐሳቦችንማሰራጨት፣ የዘር መድሎን እና ዘርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች የጥላቻ ንግግር ስለመሆናቸው ደንግጓል።ዘርን መሰረት አድርገው ከሚነሱ የጥላቻ ንግግሮች በተጨማሪ የተለያዩ ቡድኖችን ሃይማኖቶችን መሰረት አድርገው የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እዚህ ውስጥ ይካተታሉ።
እንግዲህ ሐሳብን በነጻነት መግለጽ ወደ ጥላቻ ንግግር ተሸጋገረ ለመባል የሚበቃው ዘርን፣ ሃይማኖትን እናቡድኖች ላይ ማነጣጠር ሲጀምር ነው። እንዲሁም ሁሉም በህግ ፊት በእኩልነት የመታየት መብቱሳይከበርለት ሲቀር፣አንድን ዘር ከሌላው ጋር በእኩል የመታየት መብቱ ሲነፈግ የጥላቻ ንግግር ሰለባስለመሆኑ ይታመናል።
በሌላ በኩል የጥላቻ ንግግር ከሐሰተኛ ዜናዎች ጋር የጠበቀ መመሳሰልም አለው። የሰዎችን አመለካከትለመቀየር፣ መረጃዎችን ለማዛባት፣ ማህበረሰብን ከማህበረሰብ ጋር ለማቃቃር በእቅድ የሚፈበረኩ ሐሰተኛዜናዎች በውስጣቸው በቀጥታና በተዘዋዋሪ የጥላቻ ንግግሮችንም ያሰራጫሉ። እንዲሁም የተለያዩ የፖለቲካአመለካከት ያላቸው ቡድኖችና ፓርቲዎች የፖለቲካ መሰረታቸውን ለማስፋት ማህበራዊ ሚዲያው ላይተዓማኒት የሌላቸው በጥላቻ ንግግር የታጨቁ ሐሰተኛ ዜናዎችን እንደሚያሰራጩ ይታመናል።
በጥቅሉ የጥላቻ ንግግር ወንጀል የሚሆነው እና የሚያስቀጣው በሚል በዓለም አቀፍ ተቋማት የቀረቡትቅድመ ሁኔታዎች ተጠቃለው ሲታዩ ስድስት መሰረታዊ ጉዳዮችን ይዘዋል። እነሱምመልዕክቱ የተላለፈበትከባቢ(Context)፣ የተናጋሪው ማንነት፣ የተናጋሪው የወንጀል ሀሳብ(intent)፣የንግግሩ ይዘት፣ የንግግሩተደራሽነት እና የንግግሩ ውጤት ናቸው። በተጨማሪም አንድ የጥላቻ ንግግር እንዲያስቀጣ ንግግሩየተደረገበትን ጊዜ እና ሁኔታ መመልከት ያስፈልጋል።
በተለያዩ የዓለም ሀገራት ማኀበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም የጥላቻ ንግግሮችን የሚያስተላልፉ ግለሰቦችናጥላቻ የሚሰራጭባቸው ሚዲያዎችን በህግ ፊት ተጠያቂ የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን መሰረትአድርገው ህጎችን በስራ ላይ አውለዋል። በአህጉር ደረጃ የአውሮፓ ህብረት ተጠቃሽ ነው። ከሀገራቱመካከልም ደግሞ የፀረ ሴማዊነት ጥላ የሚከተላት ጀርመን ዋነኛ ነች። ጀርመን የጥላቻ ንግግር የተላለፈበትማህበራዊ ሚዲያ በ24 ሰዓታት ውስጥ መልዕክቱን ከገጹ ላይ ካላነሳ ጠንከር ያለ ቅጣት ትጥላለች።
ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮችን የሚቆጣጠር ህግአላወጣችም። ሆኖምየፀረ-ጥላቻ ንግግር የወንጀል ሕግ ለማውጣት ረቂቁ ላይ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው።በረቂቅ ህጉ ላይ እንደተገለጸው የጥላቻ ንግግር ማለት የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይምማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ውጫዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ ፣ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ንግግር ነው በማለት አስፍሯል።
ከዚህ አለፍ ሲልም ረቂቁ አገልግሎት ሰጪ የሆኑ ማኀበራዊ ሚዲያዎችንም የሚመለከት ግዴታዎችንአስቀምጧል። በዚህም ማህበራዊ ሚዲያዎች የተከለከሉ የፀረ ጥላቻ ንግግሮች እንዳይተላለፉ ወይምእንዳይሰራጩ የመቆጣጠርና የመግታት፣ እንዲሁም ጥቆማ ሲደርሰውና ጥቆማው አሳማኝ ሲሆን ንግግሩንበአፋጣኝ የማስወገድ ወይም ከስርጭት የማስወጣት ግዴታ እንዳለባቸው ይጠቅሳል።
በዓለም አቀፍ ህግጋትና በረቂቁ ላይም እንደተነሳው ዋነኛው የጥላቻ ንግግር ማጠንጠኛ ዘርን መሰረትያደረገ ነው። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ደግሞ ዘርን መሰረት በማድረግ የተዋቀረው የፖለቲካኃይል ሀገሪቷን መምራት ከጀመረ ሩብ ምዕተ ዓመትን ተሻግሯል። በነዚህ ዓመታት ታዲያ የተለያዩግለሰቦች፣ ቡድኖችና ብሄሮች በተቀነባበረ መልኩ የጸረ ጥላቻ ንግግር ሰለባ ስለመሆናቸው በተለያየ መልኩይነሳል። በተጨማሪም የፖለቲካ አውዱ ለጥላቻ ንግግሮች መስፋፋት ምቹ ግራውንድ ስለመሆኑምይጠቀሳል።
በርግጥ ከአምስት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በኦክስፎርድ ዪኒቨርስቲ አማካኝነት በጋራ ከተሰራአንድ ጥናት በስተቀር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰነዘሩ የጥላቻ ንግግሮች በሚመለከት በኢትዮጵያተጽዕኗቸው የት ድረስ እንደሆነ ማወቅ የሚያስችሉ ጥናቶች የሉንም። ሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች ያጠኑትጥናትም በጊዜው የጥላቻ ንግግር ማህበራዊው ሚዲያ ላይ የስጋት ደረጃ ላይ ያለመድረሱን አንስተዋል።በተጨማሪም ከላይ ላነሳነው ነጥብ ማረጋገጫ መሆን የሚችል በወቅቱ ስላንዣበቡት የጥላቻ ንግግሮችመነሻም የፖለቲካ አውዱ ስለመሆኑ አስፍሯል። በዚህም ዋነኛ መነሻቸው ዋልታ ረገጥ የሆኑ የፖለቲካኃይሎች የድጋፍ መሰረታቸውን ለማስፋት የጥላቻ ንግግሮችን እንደሚጠቀሙ በጥናቱ አካቷል። በርግጥ በወቅቱ በኢትዮጵያ የነበረው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር ከጠቅላላ ህዝቡ ከ2 በመቶ በታች ነበር።በአሁኑወቅት ደግሞ ከ15 በመቶ በላይ ደርሷል። የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚው ቁጥርም በዚያው ልክጨምሯል።
ከማኀበራዊ ሚዲያ በተጨማሪ በአደባባይ ለብዙኀኑ የሚቀርቡ ንግግሮች ላይ ከፍተኛ መንግሥትባለስልጣናት እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ስማቸው በተደጋጋሚ ይነሳል። እነዚህ የአደባባይ ንግግሮችም ወደማኀበራዊ ሚዲያው በሚመጡበት ወቅት በስፋት የመሰራጨት ዕድል እንደሚያገኙ ይታመናል።
ወደ መፍትሔው ስናዘግም በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥላቻ ንግግር ለመከላከል የተለያዩ ነጥቦች ተነስተዋል።ከነዚህ መካከልም በግንባር ቀደምትነት የሚነሳው የመናገር ነጻነትና የእኩልነት መብትን በማይጻረር መልኩየፀረ-ጥላቻ ንግግር ህግ ማርቀቅ ዋነኛው ነው።
በአንጻሩ አርቲክል19 በስድስት የአውሮፓ ሀገራት በሰራው አንድ ጥናት ህግ ማውጣቱ እንዳለ ሆኖ ሀገራትየጸረ ጥላቻ ንግግር ህግ ማርቀቃቸው ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ ጥቅም እንደማያመጣ ዳሷል። ከዚህ አለፍ ሲልምድንጋጌው በጊዜ ሂደት የመናገር ነጻነትና የእኩልነት መብትን እንደሚሸረሽር ያትታል። የተነሱትን ችግሮችለመቅረፍ ጥናቱ እንደመፍትሔ ካሰቀመጣቸው ዋነኛ ጉዳዮች መካከል የእኩልነት መብትን በስፋት ማሳወቅ፣ሁሉን አቀፍ ውይይቶችን ማካሄድ በባህሎች መካከል ያለውን መስተጋብር ላይ የጋራ መግባባቶችእንዲፈጠሩ ማድረግ የጥላቻ ንግግር እንዲቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጠቅሷል።እንዲሁም የሲቪል ማህበራት ማህበረሰቡን በማንቃት ግንዛቤን ወደፊት ሊያራምዱ የሚችሉ የተለያዩፕሮግራሞችን በመቅረጽ የጥላቻ ንግግርን መቀነስ እንደሚቻልም በጥናቱ ዳሷል።
በተጨማሪም በተለያዩ መልኮች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን ከህግ ውጪ በምን መከላከል ይችላልየሚለው ሐሳብ ሲነሳ ከሚቀርቡት መፍትሔዎች መካከልም ህግ ከማውጣት በፊት ግለሰቦችና ቡድኖችግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ቀዳሚው ተግባር ነው። ግንዛቤ ሲባል መገናኛ ብዙኀን በጉዳዩ ዙሪያ የጥላቻንግግርን በመለየት ምላሽ መስጠት እንደሚገባቸው ይነሳል። እንዲሁም ብዝኀነት ላይ ያተኮሩ ስራዎችንመስራት የጥቃቱ ሰለባዎች የደረሰባቸውን ግፍ እንዲናገሩ ማበረታት በተጨማሪም ግለሰቦች ቡድኖችያላቸውን መብቶች ማሳወቅ ተጠቃሽ ናቸው። ከዚህ አለፍ ሲልም መገናኛ ብዙኀን ሐቅን የሚያጣሩፕሮግራሞችን በማካተት የጥላቻ ንግግርን መሰረት ያደረጉ ሐሰተኛ መረጃዎችን በመለየት ለማህበረሰቡቢያደርሱ ጉዳቱን መቀነስ ይቻላል።
በሌላ በኩል እንደ ትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩትዩብ ያሉ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎች ለተጠቃሚዎቻቸውከሚያወጧቸው መመሪያዎችና ግዴታዎች በተጨማሪ በደንበኞቻቸው የሚሰራጩትን የጥላቻ ንግግሮችየሚቆጣጠሩ ሰው ሰራሽ የማሰብ አቅም ያላቸው ፕሮግራሞችንና በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚሰሩአቃቢያነ-ይዘት(content moderators) ቢያሰማሩ የጥላቻ ንግግርን ለመቀነስ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣይችላል። በመጨረሻም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ግለሰቦች የጥላቻ ንግግሮችን በሚያሰራጩበት ወቅትለግለሰቡ ለራሱ ያስተላለፈው ይዘት የሌሎችን መብት የሚጋፋ መሆኑን ማሳወቅ፣ ለአገልግሎት አቅራቢውመልዕክት መላክ፣ የስጋት ደረጃው ከፍ የሚል ከሆነ ለተቋማት ማሳወቅ፣ ለሌሎች ተጠቃሚዎች ማጋራትእንዲሁም እያንዳንዱ ግለሰብ ማኀበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያስተላልፈው መልዕክት ሃይማኖትን፣ ዘርን፣ቡድንን እና ሌሎችንም ለጥቃት የሚያጋልጥ ይዘት ስለማተሙ መጠንቀቅ ቢቻለው የጥላቻ ንግግርንለመቀነስ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ።
ይሄ ፅሁፍ የጥላቻ ንግግርን እና ሐሰተኛ መረጃ በኢትዮጲያ ያለበትን ሁኔታ ቅርጽ ለመስጠት በሰባ ደረጃ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ኃላ.የተ.የግል ማኅበር፣ የአዲስ ዘይቤ እና ጎበና መንገድ አታሚ እና በኢንተርኒውስ፣ የሚዲያ ተቋማት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ዜናዎችን እና መረጃዎችን እንዲያዘጋጁ ማገዝን አላማው ያደረገ ለትርፍ ያልተቋቋመ አለም አቀፍ ድርጅት ትብብር የሚዘጋጁ ተከታታይ ግንዛቤ ማስጨበጫ የሚዲያ ውጤቶች አካል ነው፡፡©በሰባ ደረጃ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ኃላ.የተ.የግል ማኅበር2012 ዓ.ም.