ጳጉሜ 3 ፣ 2012

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጠናቀቁን ተከትሎ የህዝብ ታክሲዎች በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

ቃለመጠይቆችወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎችበብዛት እየተወራ ያለጉዳይ

በነሀሴ 30 2012 ዓ.ም ለአምሰት ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጠናቀቁን ተከትሎ በአብዛኛው የ ሃገሪቱ አካላት ላይ ለውጥ የሚያመጡ ማሻሻያዎች…

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጠናቀቁን ተከትሎ የህዝብ ታክሲዎች በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
በነሀሴ 30 2012 ዓ.ም ለአምሰት ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጠናቀቁን ተከትሎ በአብዛኛው የ ሃገሪቱ አካላት ላይ ለውጥ የሚያመጡ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የከተማዪቱን የትራንስፖርት ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት ማሻሻያው የተደረገ ሲሆን ውሳኔው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ ከተሞች ላይ የሚተገበር የሆናል።በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ትልቅ ሚናን የሚጫወቱት የህዝብ ታክሲዎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ተከትሎ በመጋቢት ወር የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጠናቀቁ ምክንያት በሙሉ አቅማቸው ማለትም ባላቸው የ ወንበር ልክ ለተሳፋሪዎች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የተለያዩ የአይን እማኞች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል። ይህንንም መረጃ በመያዝ አዲስ ዘይቤ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የ ትራፊክ ፖሊስ አናግሮ ነበር “ሁሉም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት በወንበራቸው ልክ መጫን ይችላሉ። የግል ተሽከርካሪዎችም እንዲሁ በተፈቀደላቸው የመጫን ቁጥር ማለትም ከአዋጁ በፊት እንደሚጠቀሙት መቀጠል ይችላሉ” ብሎ ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል።የትራንስፖርት ቢሮው ውሳኔውን ለማህበረሰቡ ከማሳወቁ በፊት አዲስ ዘይቤ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለፁት ከሆነ በከተማዋ የሚገኙት ታክሲዎች በሙሉ የመጫን አቅም ሰዎችን እያስተናገዱ ቢሆንም በአንዳንድ ቦታዎች ግን ከታሪፍ ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደተስተዋሉ ገልፀው የነበረ ቢሆንም በዛረው ለት በጷግሜ 03 ቅን 2012 ዓ.ም በተደረገ መረጃ ስብሰባ በአጎና አካባቢ ያሉ የተለያዩ የታክሲ ተገልጋዮች በተናገሩት መሰረት ታሪፉ መስተካከሉን ተናግረዋል። በአካባቢው ላይ የነበሩ የትራፊክ ፖሊሶችም ለታክሲ ሹፌሮች በታደሰው ታሪፍ መሰረት አገልግሎት እንዲሰጡ ሲያስጠነቅቁ ተስተውለዋል። አዲስ ዘይቤ በጉዳዩ ዙርያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮን ለማነጋገር ቢሞክርም የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

አስተያየት