ጳጉሜ 3 ፣ 2012

ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአገሪቱ የሚገኙ ሴቶችን መብት ለማሳደግ የሚውል ድጋፍ አገኘች

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

የኢትዮጵያ መንግስት፣ የቡሩንዲ መንግስትና የሃይቲ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ከሆነው ዘ ኢንተርናሽናል ቴሌኮምኒኬሽን ዩንየን (The…

ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአገሪቱ የሚገኙ ሴቶችን መብት ለማሳደግ የሚውል ድጋፍ አገኘች
የኢትዮጵያ መንግስት፣ የቡሩንዲ መንግስትና የሃይቲ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ከሆነው ዘ ኢንተርናሽናል ቴሌኮምኒኬሽን ዩንየን (The International Telecommunication Union) ከተሰኘው ኤጀንሲ ድጋፍ ማግኘታቸውን ሲኤጄ ኒውስ (CAJ News) የተሰኘው የዜና አውታር በትላንትናው እለት ዘገበ። ድጋፉ በአገራቱ የሚገኙ ሴቶችን ፍትሀዊ የቴሌኮሚኒኬሽን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚረዳ የገለፀው ዘገባው አክሎም ይህን በማድረግ በአገራቱ የሚገኙ ሴቶችን መብትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትልቅ ሚናን እንደሚጫወትም በዘገባው አስረድቷል። በተጨማሪም ድጋፉ የጨርቃጨርቅ ምርትን ጨምሮ በቡና ምርት እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ሴቶችን ለማሳተፍ አቅዶ የተነሳ ሲሆን የፕሮጀከቱን አላማ ለማሳካት ከሀገራቱ መንግስታት ጋር አብሮ በመስራት እና የተለያዩ ፖሊሲዋችን በመንደፍ እንደሚሰራ ዘገባው አክሎ ያስረዳል። ኢንተርናሽናል ቴሌኮምኒኬሽን ዩንየን በ1857 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በአለም ላይ ከሚገኙ እድሜ ጠገብ አለምአቀፍ ድርጅቶች መካከል አንዱ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ። መቀመጫውን በጄኒቫ ስዊዘርላንድ ያደረገው ድርጅቱ ከ2006 ዓ.ም አንስቶ በቻይናዊው ሆውሊንግ ዣዎ ዋና ፀሀፊነት እየተመራ ይገኛል።  

አስተያየት