ጳጉሜ 3 ፣ 2012

ኢትዮጵያ ወደታጁራ ወደብ የሚወስድውን የመንገድ ፕሮጀክት አጠናቀቀች

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎችበብዛት እየተወራ ያለጉዳይ

ኢትዮጵያ የታጁራን ወደብን ለመጠቀም የሚያስችላትን የመንገድ ፕሮጀክት በስኬት ያጠናቀቀች ሲሆን በአፋር ክልል እየተካሄደ የነበረው የመንገድ ግንባታ ከዲቾቶ…

ኢትዮጵያ ወደታጁራ ወደብ የሚወስድውን የመንገድ ፕሮጀክት አጠናቀቀች
ኢትዮጵያ የታጁራን ወደብን ለመጠቀም የሚያስችላትን የመንገድ ፕሮጀክት በስኬት ያጠናቀቀች ሲሆን በአፋር ክልል እየተካሄደ የነበረው የመንገድ ግንባታ ከዲቾቶ ተነስቶ በጋዳፊ መገንጠያ ዶቤኤል ዳር በኩል ወደ በልሆ የሚዘልቅ እንደሆነን የኢትዮጵያ መንገድ ባለስልጣን አስታውቋል።መንገዱ 78 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በገጠር ውስጥ ግራ እና ቀኝ ትከሻው 10 ሜትር እና በከተማ ኤልዳር ደግሞ 21.5 ሜትር ስፋት እንዳለው መረጃው ያስረዳል። ይህ በ2.4 ሚሊዮን ብር በጀት የተሰራው መንገድ ወጪው ሙሉ በሙሉ በመንግስት የተሸፈነ ሲሆን በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተቋራጭነት እንደተሰራም ባለስልጣኑ ገልጿል። አባይ ማለዳ የተሰኘው የዜና አውታር በዛሬው ውለት እንደዘገበው ከሆነ መንገዱ ሙሉ በሙሉ በሲሚንቶ ኮንክሪት የተገነባ ሲሆን ይህምበአከባቢው ያለውን የአየር ሙቀት ተቋቁሞ ለረጅም አመት እንዲቆይ በማሰብ ነው። መንገዱ ወደአዲሱ የታጁራ ወደብ መዳረሻ ከመሆኑም በተጨማሪ ወደ አሰብ ወደብም ይዘልቃል ያለው ዘገባው አክሎም ይህ መንገድ በመገንባቱ ወደ ጅቡቲ ወደብ ለመሄድ የነበረውን የትራንስፖርት መጨናነቅ በእጅጉ ይቀንሳል። በተጨማሪም በአከባቢው የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት በቀላሉ ወደ ለማድረስ እንደሚረዳ ባለስልጣኑ አክሎ ገልጿል። 

አስተያየት