ነሐሴ 29 ፣ 2012

የኢትዮጵያ መንግስት በትምህርት ላይ አተኩሮ ከሚሰራው አለምአቀፍ ድርጅት የስራ ማካሄጃ ድጋፍ አገኘ

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎችኹነቶች

የኢትዮጵያ መንግስት ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኤጁኬሽን (Global Partnership for Education) ከተሰኘው ድርጅት የ540 ሚልዮን ብር…

የኢትዮጵያ መንግስት በትምህርት ላይ አተኩሮ ከሚሰራው አለምአቀፍ ድርጅት የስራ ማካሄጃ ድጋፍ አገኘ
የኢትዮጵያ መንግስት ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኤጁኬሽን (Global Partnership for Education) ከተሰኘው ድርጅት የ540 ሚልዮን ብር (14.85 ሚልዮን ዶላር) የስራ ማስኬጃ ድጋፍ እንደተቀበለ ሲኤንቢሲ አፍሪካ (CNBC Africa) ዘገበ። ድጋፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ የሚያስከትለውን ተጽኖ ለመቀነስና መንግስት በወቅቱ በትምህርት ዙርያ ለሚሰራቸው ስራ ማስኬጃ እንደሚሆን ዘገባው አክሎ አስረድቷል።እንደዘገባው ከሆነ ከላይ የተጠቀሰው ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስት የትምህርት ሚንስቴር ከአዲሱ የትምህርት አምት አስቀድሞ የሚደረጉ ቅድመ ሁኔታዋች ጨምሮ የተለያዩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለማዘጋጀት የሚውል ሲሆን በአገሪቱ በወረርሺኙ አማካኝነት በትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚስተዋለውን ጫና ለመቀነስ ይረዳል።የተለያዩ መረጃዎችን እንደሚያሳዩት ከሆን በኮሮና ወረርሺኝ የተነሳ ትምህርት ቤቶች ከመጋቢት ወር አንስቶ ተዘግተው እንዲቆዩ መደረጉን ተከትሎ 26 ሚልዮን የሚሆኑ ኢትዮጲያዊያን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የቀሩ ሲሆን የአገሪቱ የትምህርት ሚንስቴር ለመጪው ትምህርት ቤቶች ለመጪው አዲስ የትምህርት አመት ተማሪዎችን ለጊዜው እንዳይመዘግቡ መግለፁ የሚታወስ ነው።ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኤጁኬሽን (Global Partnership for Education) በትምህርትና የትምህርት ማስተማር ሂደትና ጥራት ዙርያ ከተመሰረተበት 1994 ዓ.ም ጀምሮ ከሰባ በላይ በሚሆኑ አገራት በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ትምህርት ነክ ጉዳዮች ላይ አብሮ ሲሰራ ቆይቷል።

አስተያየት