ነሐሴ 29 ፣ 2012

ኢትዮጵያዊ መልክ ያለው በርገር በዋሺንግተን ዲሲ

ዜናዎችፊቸር

የአሜሪካ መዲና በሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ከሰሞኑን የተከፈተው አዲሱ ሜላንዥ (mélange) የተሰኘው ምግብ ቤት በዶሮ ወጥ ላይ የተመሰረተ…

ኢትዮጵያዊ መልክ ያለው በርገር በዋሺንግተን ዲሲ
የአሜሪካ መዲና በሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ከሰሞኑን የተከፈተው አዲሱ ሜላንዥ (mélange) የተሰኘው ምግብ ቤት በዶሮ ወጥ ላይ የተመሰረተ በርገር ለገበያ እንደሚያቀርብ አስተዋወቀ። በተወዳጁ የኢትዮጲያ ባህላዊ ምግብ “ዶሮ ወጥ” ላይ ተመስርቶ የሚዘጋጀው በርገር በአሰራሩ በአይነቱ ልዩ እና ያልተለመደ እንደሆነ ለዘ ዋሺንግቶንያን የተናገረው ሼፍ ኤልያስ ታደሰ ስለ በርገሩ አሰራር ሲያስረዳ “በርገሮቹ የሚዘጋጁት ባህላዊ የስልስ አሰራር ሂደትን በመጠቀም ነው። በተለያየ የባህላዊ ቅምማት የሚዘጋጁ የተለያዩ ማባያዎችም ይኖራቸዋል” በማለት ተናግሯል።ሼግ ኤልያስ አክሎም ከአዲሱ ፈጠራ ያለው አላማ አገርን ለማስተዋወቅና የኢትዮጵያ የምግቦ አይነቶችን ለተቀረው አለም በተለየ መልኩ ለማቅረብ እንጂ የባህሉን ይዘት ለመቀየር እንዳልሆነ የተናገረ ሲሆን በተጨማሪም በጾምና በፍስግ ወቅቶች የሚቀርቡ በተለያዩ ኢትዮጵያዊ የምግብ አይነቶች ላይ የተመሰረቱ የበርገር አይነቶችንም ይዞ ለመቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለዘ ዋሽንግቶንያን ተናግሯል።የምግብ ቤቱ ዋና ሼፍ የሆነው ሼፍ ኤልያስ ታደሰ ትውልዱ አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን በፈረንሳይ አገር በሚገኘወ ፖል ቡከስ (Paul Bocuse) የምግብ አሰራር ትምህርት ተቋም ውስጥ በምግብ ዝግጅት ትምህርቱን እንደተከታተለ ከተለያዩ መረጃዎች መረዳት የሚቻል ሲሆን የምግብ ባለሙያው በተለያዩ ታዋቂ የፈረንሳይ ምግብ ቤቶች ውስጥ በምግብ ዝግጅት ሙያ እንዳገለገለ እነዚሁ መረጃዎች ያሳያሉ።በአሜሪካ እና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በቆየባቸው ጊዜያት ያካበተውን ልምድ በመጠቀም ኢትዮጲይን ባህላዊ አመጋገብ ስርአት በባህር ማዶ ላሉ ሀገራት ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀው ይህ የፈጠራ ውጤት በዛሬው እለት ስራየሚጀምር ሲሆን ምግብ ቤቱ የተጠበሰ ዶሮ ሳንድዊች ያዞ ለመሄድ የሚያመቹ ተደርገው እንደሚ ዘጋጁ ተናግሯል።የምግብ ዝግጅት ባለሙያውን የረጅም አመት የስራ ልምድና በአይነቱ ልዩ የሆነውን የኢትዮጵያውያንን የምግብ አሰራርና አቅራረብ በማጣመር የአገሪቱን የምግብ አይነቶች ለተቀረው አለም ለማስተዋወቅ ወጥኖ የተነሳው የሼፍ ኤልያስ የምግብ ፈጠራ ከዛሬ ጀምሮ በ 2200 ቨርማንት አቬኑ (2200 Vermont Avenue)ላይ በሚገኘው ሜላንዝ በርገር በተሰኘው ምግብ ቤት መቅረብ ይጀምራል።የበርገሩ መጠርያ ዘ ናሽናል (The National) ሲሆን ዋጋው 475 ብር ወይም 13 የአሜሪካ ዶላር እንደሆነ የበርገር ቤቱ ሜኑ ያሳያል። በተጨማሪም በሬስቶራንቱ በተመሳሳይ ዋጋ የሚሸጥ ዘ በያይነቱ (The Beyaynetu) የተሰኘ ሌላ በኢትዮጵያውያን የምግብ አሰራር ላይ የተመሰረተ የበርገር ምርጫ እንዳለም ከሬስቶራንቱ ሜኑ መረዳት ይቻላል።ፎቶ፡ ከዋሺንግተን ኢተር (Washington Eater) የተወሰደ

አስተያየት