ሰኔ 16 ፣ 2010

በፍንዳታ መርሐ ግብሩ ቢቋረጥም ሰልፈኛው መፈክሩን አሰምቶ ተበትኗል

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዓሊን ለመደገፍ “ለውጥን እንደግፍ፣ ዴሞክራሲን እናበርታ” በሚል መሪ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ሚሊዮኖች በመስቀል…

በፍንዳታ መርሐ ግብሩ ቢቋረጥም ሰልፈኛው መፈክሩን አሰምቶ ተበትኗል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዓሊን ለመደገፍ “ለውጥን እንደግፍ፣ ዴሞክራሲን እናበርታ” በሚል መሪ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ሚሊዮኖች በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ድጋፋቸውን ሲሰጡ ውለዋል፡፡ የሰልፉ ተሳታፊዎች ከአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ካሉ ከተሞች የመጡ ዜጎች ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመሆን በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል፡፡ዶ/ር ዐቢይ ባደረጉት ንግግርም ከፊታችን እንደተራራ የቆመውን ችግር ሳናስወግድ እንዲህ ያለውን ምስጋና ለመቀበል የሚያስችል አቅም የለንም ብለዋል፡፡ አክለውም እንደእግር ኳስ ህዝቡ ደጋፊ እኛ ተጫዋች የምንሆንበት አይደለም፣ ህዝቡም የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡“ፅጌረዳውን ከእሾህ ለዩ፣ በአንድ ጠማማ ዛፍ ምክንያት ደኑ አይለቅ አይጥ በበላ ዳዋ አይመታ” በማለት ጅምላ ፍረጃ እንዳይኖር ሰልፈኛው መክረዋል፡፡ንግግራቸውን ከጨረሱ እና አንድ የመዝጊያ ፕሮግረም ብቻ ሲቀር በፈነዳው የእጅ ቦምብ ምክንያት መርሐግብሩ ተቋርጧል፡፡ ቦምቡ የፈነዳው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነበሩበት መድረክ በግምት 40 ሜትር ርቀት ላይ ነው፡፡ጉዳቱን በተመለከተ የተለያዩና አወዛጋቢ መረጃዎቸ እየወጡ ይገኛል፡፡ምንም እንኳን የጎበና ምንጮች የሞተ ሰው የለም ቢሉም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ የተለያዩ ሚዲየዎች የሞቱ ሰዎቸ መኖራችውን ሲገልፁ ተሰምተዋል፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፍፁም አረጋ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገጻቸው እንደገለፁት እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ማለፉን አረጋግጠዋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒሰትሩ አሚር አማን(ዶ/ር) በፌስቡክ ገፃችው በሰጡት መግለጫ በአደገኛ ሁኔታ የተጎዱት ሰዎች 8 መሆናቸውን ገልፀው በጠቅላላውም በተለያዩ የህክምና ተቋማት የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙ ተጎጂዎች ቁጥርም 140 መሆኑን ገልፀዋል፡፡ሰልፈኛው ፍንዳታው እንደተሰማ የመደናገጥ ስሜት ቢታይበትም ወዲውኑ ወደሰልፈኝነቱ ተመልሷል፡፡  እንግዶቹ በመሄዳቸው ምክንያት ባዶ የሆነው መድረክ ላይ ወጣቶች ብዙ ሆነው በመውጣት ሲጨፍሩ እና መፈክር ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡

አስተያየት