ሰኔ 10 ፣ 2010

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

ዐርብ ሰኔ 8፣2010 ዓ.ም በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ በተቀሰቀሰው አመጽ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር፣ፋይናስ እና የሰው ሃብት ቢሮዎች በእሳት…

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት
ዐርብ ሰኔ 8፣2010 ዓ.ም  በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ በተቀሰቀሰው አመጽ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር፣ፋይናስ እና የሰው ሃብት ቢሮዎች በእሳት ጋይተዋል፡፡ በተጨማሪም የፕሬዝዳንቱ እና የምክትል የፕሬዝዳንቱን ጨምሮ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በእሳት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡የተለያዩ ቢሮዎች ፣ እንዲሁም የሴት ተማሪዎች መኖሪያ ዶርምተሪዎች መዘርፋቸውን ታማኝ ምንጮች ለጎበና  ተናገርዋል፡፡በጊቢው ውስጥ የቀሩት የመጀመሪያ እና ተመራቂ ተማሪዎች መካከል በዝርፊያው ሴት ተማሪዎች በራቸው በመሰበሩ እንዲሁም ለደህንነታቸው ባደረባቸው ስስጋት ከወንድተማሪዎች ጋር ለማደር ተገደዋል፡፡አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ለጎብና እንደተናገረው የሴት ተማሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ፤የእጅ ስልኮች እና አልባሳት እንደተዘርፉ ነገር ግን በተማሪዎቸ ላይ የደረሰ ምንም አይንት የአካል ጉዳት አለመኖሩንም ጨምሮ ገልጿል፡፡ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ 11 አመት ያስቆጠረ ሲሆን የዚህ አመት ተማሪዎችን ለማስማረቅ ያስገነባው እና አዳራሽም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበትም ታዉቋል፡፡ አዳራሹም የወደመው ገና ርክክብ ከመደረጉ በፊት እንደሆነ ምንጮች ለጎበና ገልፀዋል፡፡፡በተጨማሪም የሶዶ ግብርና እና ምርምር ኮሌጅ፣ የወላይታ ዞን ግብርና እና አሳ ሃብት መምሪያ፣ የአራዳ ክፍላከተማ ጽ/ቤት፣በወላይታ ዞን የኦሞ ማይክሮ ፋይናስ ጽ/ቤት፣ የከተማው ከንቲባ ቢሮ ውስጥ ቆመው የነበሩ 60 ባለሁለት እግር ተሸከርካሪዎች የጥቃቱ ሰለባዎች ነበሩ፡፡በሃዋሳ ከተማ የነበረውን የወላይታ ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት መንግስት አስፋላጊውን ምላሽ እንዲሁም ጥበቃ አላደርገም በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት የተጀመረው እንቅስቃሴ መልኩን ቀይሮ የተለያ የንግድ ቦታዎችን ወደ ማጥቃት ተቀይሯል፡፡አርብ ጠዋት የተጀመረውን ግጭት ለመረጋጋት አርፍዶ የደረሰው የፌደራል ፖሊስ፣መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የክልሉ ልዩ ፖሊስ ከተማዋን ያረጋጋ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ትከትሎም ፍጹም ሰላም ተስተውሏል፡፡

አስተያየት