ሚያዝያ 17 ፣ 2011

ኢትዮጵያ በራንሰምዌር ጥቃት እና በክሪፕቶከረንሲ አደን እየመራች ነው

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

ባሳለፍነው የፈረንጆች አንድ ዓመት የራንሰምዌር(Ransomware) ጥቃቶች የሚሰነዘሩበት እና ክሪፕቶከረንሲ(cryptocurrency) ከሚታደንባቸው ሀገሮች…

ኢትዮጵያ በራንሰምዌር ጥቃት እና በክሪፕቶከረንሲ አደን እየመራች ነው
ባሳለፍነው የፈረንጆች አንድ ዓመት የራንሰምዌር(Ransomware) ጥቃቶች የሚሰነዘሩበት እና ክሪፕቶከረንሲ(cryptocurrency) ከሚታደንባቸው ሀገሮች መካከል ኢትዮጵያ በቁንጮነት መቀመጧን ማይክሮሶፍት ያወጣው የደኅንነት ሪፖርት ገልጿል፡፡ኢትዮጵያ ቬንዝዌላ፣ ማይናማር፣ ካሜሩን፣ እና ሞንጎልያን ከኋላ አስከትላ በወር በአማካኝ 0.77 የራንሰምዌር ጥቃቶች የሚያጋጥሟት ቀዳሚዋ ሀገር ሆና ተመዝግባለች፡፡ለመሆኑ ራንሰምዌር ምንድን ነው?ራንሰምዌር ማለት የሸረኛ ሶፍትዌር አይነት ሲሆን ለጥቃት ወደ ተጋለጠ ኮምፒውተር በመግባት የኮምፒውተር ስርዓቱ ወይም ሌሎች በኮምፒውተሩ ያሉ ሰነዶች በመቆለፍ የማስለቀቂያ ዋጋ (ቤዛ) የሚጠየቅ ነው፡፡ እጅግ የከፋ ጠላፊ ካጋጠመዎ ቤዛውን ወይም የተጠየቁትን ዋጋ ከከፈሉ በኋላም ሰነድዎ ወይም ስርዓተ ክወናዎ እንደተቆለፈ ሊቀር ይችላል፡፡ ይህ ሸረኛ ሾፍትዌር የሚሰራጨው በአሳሳች ኢሜሎች እና በተጠቁ መካነ ድሮች ላይ በሚደረግ ደኅነቱ ያልተጠበቀ ጉብኝት ነው፡፡አሜሪካን፣ ጃፓን እና አየርላንድ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2018 በጣም ዝቅተኛ የራንሰምዌር ጥቃቶች ከተሰነዘረባቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ የደኅንነት ሪፖርቱ የራንሰምዌር ጥቃቶች በዓለም ዙርያ እየቀነሱ መሆናቸውን ይናገራል፡፡ የማይክሮሶፍት አጥኚዎች የተጠቃሚዎች ግንዛቤ መጨመር እና የክሪፕቶከረንሲ አደን አዋጭ መሆን ለመቀነሱ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡የክሪፕቶከረንሲ አደንበተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የክሪፕቶከረንሲ አደኖች ከሚያጋጥሟቸው ሀገራት መካከል በወር በአማካኝ 5.58% በማምጣት ታንዛንያ እና ፓኪስታንን በማስከተል መሪነቱን ይዛለች፡፡ዲጂታል ገንዘብ(ክሪፕቶከረንሲ) የባንክ እና የሌሎች ገንዘብ ማስተላለፊያ አካላት ድጋፍ ሳያስፈልግ በውስብስብ የሂሳብ ቀመር አማካኝነት የሚተዳደር፣ በሁለት ሰዎች መካከል የሚደረግ የመስመር ላይ ግብይት/ዝውውር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን የሂሳብ ቀመር ለማስተዳደር ከፍተኛ የኮምፒውተር ትይይዝ ይፈልጋል፡፡ ይህንን በማቅረብ ለሚያስተዳደሩ ፈቃደኞች ስርዓቱ በራሱ ክፍያዎች ይፈጽማል፡፡ ይህም የክሪፕቶከረንሲ አደን(ማይኒነግ) ይባላል፡፡ ጠላፊዎች ሸረኛ ሶፍትዌሮችን ወደሰዎች ኮምፒውተር በማስገባት ከሰውየው እውቅና ውጪ ስርዓተ ክውናውን በመጠቀም ክሪፕቶከረንሲ ያድናሉ፡፡ ኢትዮጵያም ከፍተኛ ተጋላጭነት ማስገንዘቧ በርካታ ኮምፒውተሮች በሸረኛ ሶፍትዌር መጠቃታቸውን ያሳያል፡፡

አስተያየት