You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
(አዲስ ዘይቤ)የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን(ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት ካሣሁን ፎሎ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት አቶ አባዱላ ገመዳ በጥቅምት 24፣ 2012 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ ‘ጊዜ የማይሰጥ እና አሳሳቢ’ ሲል ኮንፌደረሽኑ ለገለጸው የድርጅቱ ሠራተኞች በማኀበር የመደራጀት ጉዳይ ቦርዱ በአምስት ቀን መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።በሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ያገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች መሠረታዊ ማኀበር ‘ያደረገው ስብሰባ ሕገ ወጥ ነው በማለት ሠራተኞቹን የተመረጡ አመራሮች አይወክሉንም በማለት እንዲፈርሙ ቢያስገድዱም ሠራተኛው ይህ ፊርማ ስብሰባ ላይ መገኘታችን እንጂ ድርጅቱ በሚለው መልኩ መስማማታችንን አይገልጽም ብለው በፊርማቸው ፊት ለፊት መጻፋቸውን’ ይህ ደብዳቤ አክሎ ገልጿል።እንዲሁም ድርጅቱ ማኅበሩ እንዳይመዘገብ አብሬም አልሠራም በማለት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱን መጠየቁን ኮንፌዴሬሽኑ ‘በየትኛውም ድርጅት ላይ ያልተፈጸመ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው’ ሲል ኮንኖታል።ኮንፌዴሬሽኑ ከመሠረታዊ የሠራተኛ ማኀበሩ አገኘኹት ያለውን የደርጅቱን ጣልቃ ገብነት የሚያሳይ አራት ገጽ ደብዳቤ በማያያዝ በነጻነት የተቋቋመውን ማኀበር እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እና አባላት እንዳይመዘገብ ማገዱ ልክ አለመሆኑን ገልጿል።በተመሳሳይ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኀበሩ አመራር “በአሠሪዬ ከፍተኛ ጫና እየደረሰብኝ ነው” በማለት ለአዲስ ዘይቤ መግለጹ ይታወሳል፡፡ ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ፡፡