You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢው በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን ያጡ አሉ፣ ቤት ንብረታቸውንም እንዲሁ፡፡ ጥቃት ሲጀመር የፖሊስ ከለላን ተማምነው ጥረው ግረው ያፈሩትን ጥቂት ንብረት ጥለው መሸሽ አልፈጉም ነበር፡፡ ነገር ግን ነገሮች እየከፉ ሲሄዱ በቻሉት አቅም ህይወታቸውን ለማትረፍ ተፍጨርጭረዋል፡፡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ አስኮ እና ኮልፌ አከባቢዎች የተሰደዱ አሉ፡፡ ገሚሱ ጫካ አድረው ህይወታቸውን ታድገዋል፡፡ ይህንን ሰብዓዊ ፍጡራንን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ዝርዘሩ በወንጀል ምርመራ ሂደት የሚታወቅ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ዜጎች ብዙ የሚናገሩት ታሪክ አላቸው፡፡ ዘይቤ ከብዙዎቹ ተጠቂዎች መካከል ጥቂቶችን በማናገር ይህንን ጽሁፍ አዘጋጅታለች፡፡ዘሜ ዘለቀ እባላለኹ፡፡ የ11 ልጆች አባት ነኝ፡፡ በቡራዮ ከተማ 23 ዓመት ኖሬያለኹ፡፡ ባለፉት አራት ዓመታት ግን ነገሮች ተቀይረዋል፡፡ ለጋሞ ማኀበረሰብ ጥላቻ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ትግሬን እናስወጣ እንጂ የእናንተ ጉዳይ ያበቃለት ነው እያሉ ያስፈራሩን ነበር፡፡ እኛ ምን እንዳደረግን አናውቅም፡፡ እንጀራ ፍለጋ የመጣን በሸማ ስራ የምንተዳደር ሰዎች ነን፡፡ እኛ በመምጣታችን በአከባቢው ልማት እንዲኖር አድርገናል፡፡ ቤታችን እየተለየ ነው ጥቃት የተሰነዘረብን፡፡ ቤቴን በሙሉ ዘርፈውኛል፡፡ አስለቃሽ ጭስ ይለቃሉ፡፡ ብዙዎች ታርደው ወንዝ ተጥለዋል፡፡ ጅብም የበላቸው አሉ፡፡ የልጆቼ ደኅንነት አሳስቦኝ ሁሉንም ነገር ጥየ ወጥቻለኹ፡፡ እዚያው የቀሩትን ወደ ጮሪሳ፣ አምቦ እና ገፈርሳ መስመር እየወሰዷቸው ነበር፡፡ ጥቂት ልጆች ከሞትንም እዚሁ እንሂድ ብለው ከመኪና ዘለው በመውረድ ጮሪሳ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተጠልለዋል፡፡ ቡራዮ ማዘጋጃ ቤትም የተጠለሉ አሉ፡፡ እኛ ወደዚህ መጥተን የአዲስ አበባ ህዝብ እየተንከባከበን ነው፡፡ እነርሱ ግን በቂ እርዳታ ያገኙ አልመሰለኝም፡፡[caption id="attachment_1242" align="alignnone" width="647"] ዘሜ ዘለቀ[/caption]ፋጤ ኡስማን እባላለኹኝ፡፡ ፊዲሮ ሶራምባ አከባቢ ነበር ቤቴ፡፡ ከዘጠኝ አመት በፊት ጀምሮ በስፍራው እየነገድኩኝ ነበር የምኖረው፡፡ የምኖርበት ቤት በብር ገዝተን ነው ከባለቤቴ ጋር የገባነው፡፡ ነገር ግን ድንጋይ እየወረወሩ ያስቸግሩን ነበር፡፡ ስልጤ እና ጉራጌ ብቻ እየመረጡ ነበር የሚደበድቡት፡፡ ቄሮዎች ወደ ቤቴ መጥተው ባለቤቴ የት እንዳለ ጠየቁኝ፡፡ ብር የት እንደሚያስቀምጥ ጠየቁኝ፡፡ እንዳማላውቅ ስነግራቸው ቤቱን ማፈራረስ ሲጀምሩ ሦስት ልጆቼን ይዤ ወጣኹኝ፡፡ 32 በጎቼን ወስደውብኛል፡፡ አከራይቼ የምተዳደርበት አምስት ቤቶች በሙሉ ተቃጥለዋል፡፡ የልጆቼ መጽሐፍት ሳይቀር በሙሉ ተቃጥለዋል፡፡ አሁንም በጄ ምንም ነገር የለኝም፡፡ አሁን እዚህ(ፈሊጶስ ትምህርት ቤት) ከመጣኹኝ በኋላ ነው ልጆቼ እንኳን ልብስ የለበሱት፡፡ አሁን ወዴት እንደምንሄድ አናውቅም፡፡[caption id="attachment_1243" align="alignnone" width="636"] ፋጤ ኡስማን[/caption]በድሪያ ኤልያስ እባላለኹ፡፡ የአንድ ልጅ እናት ነኝ፡፡ ቤሮ የሚባል ቡራዮ ውስጥ የሚገኝ ቦታ ነበር ከባለቤቴ ጋር የምኖረው፡፡ ተከራይተን መኖር ከጀመርን ሁለት ዓመት ሆነን፡ ሐሙስ ዕለት ባለቤቴ ለስራ ወጣ ብሎ ነበር፡፡ ከዚያ ደውሎ በባንዲራ ምክንያት ቤት እያቃጠሉ ነው ባለሽበት አርፈሽ ተቀመጪ አለኝ፡፡ ፈራኹኝ እና ከቤቴ ወጥቼ ወደመንገድ ሄድኩኝ፡፡ አንድ ሰውዬ “የትአባሽ ትሄጃለሽ ወደመጣሽበት ተመለሺ” ሲለኝ ተመልሺ ወደቤት ገባኹኝ፡፡ ከጎረቤቶቼ ከወላይታዎች ጋር ቂም ስለነበራቸው ቤታቸው ተቃጠለ፡፡ እሳቱን ሳይ ቅያሪ ልብስ እንኳን ሳልይዝ መንገድ ጀመረኩኝ፡፡ በመንገድ ላይ በመኪና ሲያልፉ ያስፈራሩኝ ነበር፡፡ እየፈራኝ እዚህ መጣኹኝ፡፡[caption id="attachment_1240" align="alignnone" width="606"] በድሪያ ኤልያስ[/caption]ዘኪያ ሻፊ እባላለኹ፡፡ የአንድ ልጅ እናት ስሆን አሁን የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር ነኝ፡፡ ከባለቤቴ ጋር ተከራየተን መኖር ከጀመርን ሦስት አመታችን ነው፡፡ ባለቤቴ ኢንዱስትሪ ዞን በእንጨት ሰራተኝነት ነው የሚተዳደረው፡፡ ኪራይ እንዲቀንስልን በማሰብ ነው ወደዚህ የመጣነው፡፡ ከኋላችን የወላይታዎች ቤት ነበር እርሱን በእሳት አነደዱት፡፡ ከዚያ ልንወጣ ስንል ቄሮዎች በር ዘጉብን፡፡ ከዚያ እርስ በርስ ተጣሉ፡፡ ግማሾቹ “ህጻናት አሉ፤ ይውጡ፡፡” ሲሉ ግማሹ ደግሞ “ማንም አይወጣም፡፡” ብለው ክርክር ጀመሩ፡፡ አንደኛው ገፍትሯቸው መጣና በር ከፍቶ ውጡ አለን፡፡ ምንም ሳንይዝ ከቤት ወጣን፡፡ ስለመሸ የትም መሄድ አልቻልንም ከዚያ ኢንዱስትሪ መንደር ሜዳ ላይ ልብስ ሳንለብስ አደርን፡፡ ከዚያም በንጋታው ወደ እዚህ መጣን፡፡ እናቴም ከእኔ ቤት ጎን ተከራይታ ነው ነበር የምትኖረው፡፡ ወደዚህ ከመጣን አሏህ ይስጣቸው ምንም አላጎደሉብንም፡፡[caption id="attachment_1237" align="alignnone" width="628"] ዘኪያ ሻፊ[/caption]ስሜ ራዲያ ሽፋ ይባላል፡፡ የዘኪያ እናት ነኝ፡፡ ቡራዮ መኖር ከጀመርኩኝ ወደሰባት አመት ይሆነኛል፡፡ ቤቴን አንዲት ትንሽ ልጅ ቤት አስጠበቄ ገበያ ነበርኩኝ፡፡ ድንች፣ ሽንኩት፣ ሸንኮራ እና ሌሎች ነገሮች እየሸጥኩኝ ነው የምተደዳደረው፡፡ ልጅቷን ብር አምጪ ብለው አስጨነቋት፡፡ ልጅቷ አላውቅም ስትል ቡፌውን ገለበጡት፡፡ እርሷን ጎረቤት ያሉ ሰዎች አልጋ ስር ወሽቀው አዳኑልኝ፡፡ ሦስት ልጆቼን ይዤ ወጥቼ ጫካ አደርኩኝ፡፡ ከዚያ እዚህ መጣኹኝ፡፡ ምን እንደተፈጠረ የማውቀው ነገር የለም፡፡[caption id="attachment_1238" align="alignnone" width="639"] ራዲያ ሽፋ[/caption]ኡሱ ኦሎ እባላለኹ፡፡ ከዛሬ አስራ ስድስት ዓመት በፊት ነው ከገበሬዎቹ 200 ካሬ ሜትር መሬት ገዝቼ የገባኹት፡፡ በሽመና ሙያ ነው የምተዳደረው፡፡ ከእኔ ጋር ስድስት ቤተሰብ አስተዳድራለኹ፡፡ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ጥሩ ወሬ የለም፡፡ እናንተን ሳንጨርስ ሌላውን መግዛት አንችልም ይሉን ነበር፡፡ ከረቡዕ ጀምሮ እየመጡ የቤታችንን በር እየደበደቡ እና ጣሪያችን ላይ ድንጋይ እየወረወሩ ወደጫካ ይገባሉ፡፡ ወደ ኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እየደወለን ነበር፡፡ እኛን አይመለከተንም ይሉን ነበር፡፡ እናተንተን ለመጠበቅ መንግስት ፍቃድ አልሰጠንም ይሉናል፡፡ እኛ ተጨንቀን ለልጆች እንኳን ምግብ መግዛት አልቻልንም ነበር፡፡ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስም እየደወለን ነበር፡፡ የክልሉ መንግስት ካልፈቀደ አንመጣም ይሉን ነበር፡፡ እንዲሁ ከአሁን አሁን ገብተው ጨረሱን እንዳልን ሦስት ቀን ቤታችን ውስጥ ቆየን፡፡ ቅዳሜ ሰልፉ ካለፈ በኋላ ፖሊሶች መጥተው አትጨነቁ ከአሁን በኋላ ችግር የለም አሉን፡፡ እኛም ተመስገን ብለን ለልጆች ምግብ ማብሰል ስንጀምር፡፡ ሳይታሰብ ቄሮዎቹ ገጀራ፣ ድንጋይ እና መሣሪያ እና አስለቃሽ ጭስ ይዘው መጥተው ይደበድቡን ጀመር፡፡ ስድስት ሰዎች በጥይት ተኩሰው ገደሉብን፡፡ የአስር ዓመት ህጻን ልጅም በገጀራ ታርዶ ወንዝ ላይ ተጥሎ ተገኘ፡፡ እሬሳዎችን ይዘን ስናለቅስ አደርን በንጋታው እዚህ መጣን፡፡[caption id="attachment_1241" align="alignnone" width="639"] ኡሱ ኦሎ[/caption]