You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ የተደረሰውን የሰላም እና የእርቅ ስምምነት ተከትሎ በጦርነቱ በድንበር አከባቢ ተቀበረውን ፈንጂ የማጽዳት እና የማምከን ስራ በአከባቢው ማኀበረሰብ እና በሁለቱ አገራት ወታደሮች ትብብር መጀመሩን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡የጎበና ምንጮች እንደገለፁት ዛሬ በአዲቋላና መንደፈራ ለረጅም ዓመታት ተቀብረው የቆዩት ፈንጂዎች ሲፀዱ የዋሉ ሲሆን ነገ በዛላምበሳ ይሔው የፈንጅ ማፅዳት ስራ ቀጥሎ ይውላል:: ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሁለት አመታት የቆየ እጅግ ደም አፋሳሽ ጦርነት ማካሄዳቸውን ተከትሎ ላለፊት ሃያ አመታት በድንበር ላይ ተፋጠው መቆየታቸው ይታወሳል:: በዚህ ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከሰባ ሺህ ያላነሰ እንደሞተ ይገመታል፡፡በቅርቡ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለላኩት የሰላም መልእክት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በጎ ምላሽ በመስጠታቸው የሁለቱ አገራት የመንግስታትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንደአዲስ በደመቀ መልኩ ተጀምሯል፡፡ ዐቢይ አሕመድ በኤርትራው ጉዟቸው ወቅት ያደረጉላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሦስት ቀናት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ታውቋል፡፡