በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ፍጹም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት እንደገለፁት ከሆነ ኢትዮጵያ በአሜሪካ የተወሰደውን ውሳኔ ተከትሎ እርዳታው እንዳይሰጥ የተወሰነበትን ምክንያት ከአሜሪካ መንግስት ለመስማት ለሰኞ ምሽት ሶስት ሰዓት ተኩል እንደተቀጠሩ በመልክቱ ላይ አምባሳደሩ አሳውቀዋል።ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ በትራምፕ አስተዳደር የተላለፈው ውሳኔ ብዙዎችን እንዳነጋገረ የሚታወስ ነው። ብሉምበርግ (Bloomberg) ፎሪን ፖሊሲን (Foriegn Policy) አጣቅሶ እንደዘገበው ከሆነ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሴክረተሪ ማይክል ፖምፔዮ የፈረሙት የእርዳታ ቅነሳ እቅድ ለኢትዮጵያ ፀትታ ማስከበርና ሽብርተኛነትን ለማስወገድ እንዲሁም የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርን ለመግታት ከሚተገበሩ ፕሮጀችቶች ላይ የሚቀነስ ነው። ዘገባው አክሎም ለሰብአዊ እርዳታ፣ የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከጤና ጋር የተያያዙ ድጋፎች በተጠቀሰው የእርዳታ ቅነሳ እቅድ ላይ እንዳልተካተቱ አስረድቷል።አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችው $130 ሚሊዮን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኗን ሰምተን ማብራሪያ ጠይቀናል! ማብራሪያው ለሰኞ በ2:30PMEST ተቀጥሯል! ጉዳዩ በህዝባችን ጥሪት እየተገነባ ካለው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር እንደሚያያዝ ሰምተናል:: pic.twitter.com/NOYsloBhhX
— Fitsum Arega (@fitsumaregaa) August 30, 2020
ነሐሴ 25 ፣ 2012
የኢትዮጵያ መንግስት በትራምፕ አስተዳደር የእርዳታ ቅነሳ ውሳኔ ዙሪያ ማብራሪያ ጠየቀ
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችው $130 ሚሊዮን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኗን ሰምተን ማብራሪያ ጠይቀናል! ማብራሪያው ለሰኞ በ2:30PMEST ተቀጥሯል! ጉዳዩ…