ነሐሴ 28 ፣ 2012

“ምንም የተረፈ ንብረት የለም፣ ጎርፉ ሁሉንም ነገር ወስዶታል። እስካሁን የደረሰልን አካል ግን የለም” የመተሃራ ከተማ ነዋሪ

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

በመተሃራ ከተማ ከትናንት በስቲያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በርካታ ንብረት መውደሙን የከተማው ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ገልፁ። ከሌሊት ሰባት ሰዓት አንስቶ…

“ምንም የተረፈ ንብረት የለም፣ ጎርፉ ሁሉንም ነገር ወስዶታል። እስካሁን የደረሰልን አካል ግን የለም” የመተሃራ ከተማ ነዋሪ
በመተሃራ ከተማ ከትናንት በስቲያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በርካታ ንብረት መውደሙን የከተማው ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ገልፁ። ከሌሊት ሰባት ሰዓት አንስቶ በከተማው በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ አማካኝነት የከተማው ነዋሪዎች የመፈናቀል አደጋ እንደደረሰባቸውም አዲስ ዘይቤ ያነጋገረው የመተሃራ ከተማ ነዋሪ ገልፅዋል። በመተሃራ ከተማ ሃርዋዴ ቀበሌ 02 ወይም በተለምዶ ስሙ አዲስ ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው ጎርፍ በአካባቢው የሚኖሩትን ነዋሪዎች ንብረት አንድም ሳያስቀር እንደወሰደ የተናገረው የከተማው ነዋሪ የሆነው ጂብሪል ኡመር “የአካባቢው ነዋሪዎች ጎርፉን ለመገደብ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። በዚህም ምክንያት በርካታ ንብረት ወድሟል።” በማለት ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል።የአካባቢው ነዋሪዎች ጎርፉን ተከትሎ ከመንግስት አካላት ይሄ ነው የሚባል እርዳታም ሆነ ምላሽ እስካሁን እንዳላገኙ የገለፀው ጂብሪል “ጎርፉ በተከሰተበት ወቅት ከሚመለከተው የመንግስት አካል  ነን ያሉ ግን ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች በፒካፕ መኪና መተው አካባቢውን አይተውት ነበረ። ነገር ግን ወዲያው ተመልሰው ሄደዋል።” በማለት ከመንግስት ስለተሰጠው አናሳ ምላሽ ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በጎርፉ የተጠቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ጎርፉ ወዳልደረሰባቸው ጋራማ ቦታዎች እንዲሁም ዳንዲ ጉዲያ በመባል በሚታወቀው ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ጂብሪል ለአዲስ ዘይቤ የገለፀ ሲሆን የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ህብረተሰቡን መደገፍ እንደሚገባው አበክሮ አሳስቧል። 

አስተያየት