የካቲት 19 ፣ 2014

በሶማሌ ክልል የሚገኘው የአይሻ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በቅርቡ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል

City: Somaliዜና

በሶማሌ ክልል እየተገነባ የሚገኘው የ አይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ሲጠናቀቅ 120 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን የግንባታ ስራውም በ 3 ደረጃዎች የሚከናወን ይሆናል።

Avatar: Abdi Ismail
አብዲ ኢስማኤል

Abdi Ismail is Addis Zeybe's correspondent in Somali regional state

በሶማሌ ክልል የሚገኘው የአይሻ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በቅርቡ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል
Camera Icon

Credit: texintel

በሶማሌ ክልል በመገንባት ላይ የሚገኘው የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአሁኑ ወቅት 77% መድረሱንና በቅርቡ 40 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በሶማሌ ክልል በነበራቸው ጉብኝት ገለፁ።

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከሶማሌ ክልል ውሀ ልማት ቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን በፋፈን ዞን ሸቤሌይ ወረዳ እየተገነቡ ያሉ የመጠጥ ውሃ፤ የሳኒቴሽንና የኢነርጂ ፕሮጀክቶች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በፕሮጀክቶቹ ግንባታ ላይ በርካታ ችገሮች እያጋጠመ መሆኑንና በግንባታ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችንም ለመፍታት እንደሚሠራ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የአይሻ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ገደብና በጀት እየተገነባ እንዳልሆነ የገለፁት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ ናቸው።

ከንፋስ ኃይል ማመንጫው ጋር በተያያዘ ፕሮጀክቱ የገጠመውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሥራዎችን እንደሚሠሩ ኢ/ር ሀብታሙ ጠቁመዋል።

በሶማሌ ክልል እየተገነባ የሚገኘው የ አይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ሲጠናቀቅ 120 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን የግንባታ ስራውም በ 3 ደረጃዎች የሚከናወን ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለአይሻ የኃይል ማመንጫ ግንባታ እንደ ደቸ ባንክ፣ ክሬዲት ሱሲ፣ ጄፒ ሞርጋን እና በርክሌይስ ካሉ አለም አቀፍ ባንኮች የ 1 ሚሊየን ዶላር ብድር አግኝቷል። የፕሮጀክቱን የመጀመሪያ ደረጃ ግንባታ ወጪም የቻይናው ኤግዚም ባንክ እንደሚሸፍን ስምምነቱ ያስረዳል።

እአአ በ 2020 እንሚጠናቀቅ እቅድ የተያዘለት ይህ የ 1.3 ሚልየን ዶላር ፕሮጀክት በመጀመሪያው ደረጃ 120 ሜጋ ዋት፣ በሁለተኛው ደረጃ ሌላ 120 ሜጋ ዋት እና በመጨረሻውና 3ኛ ደረጃ ግንባታው የ 60 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ማመንጫ መሰረት ልማቶችን በመገንባት ይከናወናል።

አስተያየት