ዛሬ ህዳር 6 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። መልስ የሰጡባቸውን ዓበይት ጉዳዮች በዚህ መልኩ አጠናቅረናቸዋል።
ግብርናን በተመለከተ ኢትዮጵያ፡-
- ስንዴ ወደውጪ መላክ የምትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች
- የሩዝ ምርት ከውጪ ማስገባት የምታስቀርበት አቅም ላይ ደርሳለች
- የቡና ምርት በዚህ አመት በ20% ያድጋል
- የግብርናው ዘርፍ ዋና አላማ በሬንና ገበሬን መለያየት እና በሬን ለእርሻ ማዋል ቀርቶ ማድለብ መጀመር ነው
ኢንደስትሪን በተመለከተ፡-
- የኢንደስትሪው ዘርፍ 4.9% እድገት ቢያሳይም ከአምናው ቅናሽ አሳይቷል
- “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚለው ፕሮጀክት የቆሙ ኢንደስትሪዎች ስራ ስለጀመሩ ጥሩ እመርታ አሳይቷል
አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በተመለከተ፡-
7.6% እድገት አሳይተዋል፤ ዋና ዋናዎቹ፡
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ - ከኮሮና ጊዜ ጀምሮ ተደራሽነቱ አስፍቷል
- ኢትዮቴሌኮም - በለውጡ ማግስት 37 ሚሊዮን የነበሩት ደንበኞች አሁን 68.9 ሚሊዮን ደርሰዋል
- ተደራሽነት እና ውጤታማነት ላይ ያተኩራል
- ሞባይል ባንኪንግ ከ25.5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት፤ ይህም 134 ቢሊዮን ብር በላይ የንግድ ልውውጥ እንዲካሄድ አስተዋጽኦ አድርጓል
- በርካታ የግል እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በቴሌኮም አገልግሎት መጠቀም ጀምረዋል
- የፋይናንስ ሴክተር - በ21% እድገት አሳይቷል፣ አጠቃላይ ሃብቱም 2.3 ትሪሊየን ብር ድርሷል።
- በባንክ በኩል 82.2 ሚሊየን የባንክ ደንበኞች ተፈጥረዋል
- 1.6 ትሪሊዮን ብር በባንክ ተቀምጧል
- ብድር በ29% አድጓል - 353 ቢሊየን ብር ብድር ተሰጥቷል
- ማክሮ ኢኮኖሚው ከአምናው 6.4% ወደ 7.5% አድጓል
የዋጋ ንረትን በተመለከተ፡-
- በፍላጎትና አቅርቦት መሃል ካለው ክፍተት በተጨማሪ ጦርነት አባብሶታል። ይህን ለማስተካከልና ገበያን ለማረጋጋት፡
- የእሁድ ገበያ - ገበሬው ምርቱን ይዞ የሚቀርብባቸውና ሸማቹን ቀጥታ የሚያገኝባቸው ቦታዎች ተዘጋጅተዋል
- የተማሪዎች ምገባ - ኢትዮጵያ በቀን ሁለት ጊዜ 9.5 ሚሊዮን ተማሪዎች ትመግባለች።
- አዲስ አበባ ውስጥ ምንም ገቢ የሌላቸው ከ30 ሺ በላይ ችግረኛ ሰዎች ምሳ የሚበሉበት ቦታም ተዘጋጅቷል።
ትምህርትን በተመለከተ፡-
- ላለፉት 4 አመታት አዲስ ዩኒቨርሲቲ አልተከፈተም። ወደፊትም በቅርቡ አይከፈትም። የሚያስፈልገው አጠቃላይ የትምህርት ስርዓት ለውጥ ነው።
- መዋዕለ ህጻናት በብዛት እየተከፈቱ ነው። ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ጊዜ መውጣት ያለበት ከመሰረቱ ላይ ነው።
የዋጋ ግሽበት፡-
- የገበያ ትስስር ላይ ችግር አለ። ብላቴ የሚበቅል ሙዝና ፓፓያ፣ ጨንቻ እና ጅማ የሚበቅል አፕል አዲስ አበባ ገበያ መድረስ አቅቶት ይበላሻል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ አፕል ከውጪ ታስገባለች።
- የሌማት ትሩፋት የተባለ ፕሮጀክት ተጀምሯል። ከመሰረታዊ የምግብ አቅርቦት በላይ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ላይ የሚሰራ ነው። ማር፣ ዶሮ እና እንቁላል እርባታ፣ ላምና እርባታና ወተት አቅርቦት ላይ ይሰራል።
- ሩዝ፣ ስንዴ፣ በቆሎ ምርት ላይ በስፋት እየተሰራ ነው።
- በሚቀጥሉት 4 አመታት እንደ አረንጓዴ ልማትና የከተማ ግብርና ባሉ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ አጀንዳ እንዳይሆን ይሰራል።
ለዋጋ ግሽበት መፍትሄ፦
- ምርታማነትን መጨመር
- ብክነት መቀነስ
- ማዕድ ማጋራት
- ከሌብነት መታቀብ
- ከግጭት ሰላምን መምረጥ
ከውጪ የሚገቡ ሸቀጦችን እቀባ በተመለከተ፡-
- ኢትዮጵያ ከውጪ በመደበኛ መንገድ በሚገቡ ሸቀጦች ብቻ ሸቀጦች ብሄራዊ ባንክ የሚያውቀው 18 ቢሊየን ብር ታወጣለች
- ከ 6000 በላይ ሸቀጦች ከውጪ የሚገቡ ሲሆን አሁን እቀባ የተደረገው 38ቱ ላይ ብቻ ነው
- እቀባው ለሃገር ውስጥ ምርቶች እድል ይሰጣል፤ ፍራፍሬ፣ ጭማቂ፣ ውሃ፣ ሳሙና በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ናቸው።
- እቀባው የጥቁር ገበያን ንግድ እንደሚያዳክም ይታመናል
- እቀባው መሰረታዊ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ ያተኮረ ነው
- በእቀባው የሚጎዱ ግለሰቦች ቢኖሩም እንደሃገር ግን አትራፊ ነው
ኢንቨስትመንትን በተመለከተ፡-
- ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የመንግስትም የህዝብም አይደለም፣ የደላሎች እና የሌባ ሹመኛ ሆኗል፤ ስር ነቀል ማስተካከያ ያስፈልጋል፤ ቢያንስ በከተሞች መሬት የግለሰብ መሆን አለበት።
- ኢንቨስተሮች በኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኩል ሲስተም ቢስተካከልም ለመጠቀም ተነሳሽነታቸው አነስተኛ ነው፤ የሚፈለገው መሬት ወስዶ፣ መሰረት አውጥቶ፣ ብር ከባንክ መበደር ነው። ይህ መቅረት አለበት።
የከርሰ ምድር ውሃን በተመለከተ፡-
- ኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ውሃ ሃብት አላት፤ በርካታ ፓምፕ በማስገባት የመስኖና የግድብ ስራዎች እየተሰሩ ነው
ጤናን በተመለከተ፡-
- እንደትምህርት ስራ ይጠይቃል። የግሉ ዘርፍም መሳተፍ አለበት
ስራ አጥነትን በተመለከተ፡-
- ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ አለ፣ ሰራተኛም አለ። ሁለቱን ለማገናኘት የሰራተኛና ክህሎት ሚኒስቴር እጅግ አመርቂ ስራ እየሰራ ነው።
- የቅጥር መረጃን ዘንድሮ አሳክተናል። በተዘረጋው ሲስተም መሰረት በየቀኑ ስንት ሰው ስራ አገኘ የሚለውን ማወቅ ይቻላል።
- በዚህ አመት ከ 3 ሚሊየን በላይ ሰው ስራ ለማስያዝ እየተሰራ ነው
- የህዳሴ ግድብ፣ የኮይሻ ፕሮጀክት፣ ግብርናው፣ የከተማ ህንጻ ግንባታዎች ስራ ይፈጥራሉ።
- የተማረም ያልተማረም ስራ እንዲይዝ ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም ዜጋ ስራ ካልያዘ ክላሽ ያነሳል፣ ለሃገር ፈተና ይሆናል።
ቱሪዝምን በተመለከተ፡-
- የብልጽግና አእማድ ዋናው አገልግሎት ሰጪ ዘርፉ ነው
- ላሊበላ በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እየታደሰ ነው
- ዩኒቲ ፓርክ ራሱን ችሎ ለኢዮቤልዩ ቤተመንግስትንም እድሳት እያዋጣ ነው።
- በርካታ ውድና ታሪካዊ ሃብቶችን የያዘው ኢዮቤልዩ ቤተመንግስት በሚቀጥለው አመት ለህዝብ ክፍት ይሆናል
- ጎርጎራ ፕሮጀክት እጅግ ግዙፍና ውብ ነው። ሲያልቅ በ30 ደቂቃ የሃይቅ ላይ ጉዞ ዳጋ እስጢፋኖስ መሄድና የፋሲልና ሱስንዮስን መቃብሮች የመሰሉ ታሪካዊ ቦታዎች ማየት ይቻላል
- አዲስ የተከፈተው ፓርክ በአንድ ሰንበት ብቻ ከመቶ ሺ በላይ ህጻናት ጎብኝተውታል
- የሃገር ውስጥ ቱሪዝም በዚህ አመት በ8% አድጓል
- በአዲስ አበባ ከ400-500 ቢሊየን ብር ወጪ የሳተላይት ከተማ እየተገነባ ነው። የሃገር ኩራት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ድርድሩን በተመለከተ፡-
- “የማያልቅ ጦርነት ውሃ በወንፊት ነው፤ እየተዋጉ መኖር የለም። ሰላምና ብልጽግናን ለማስቀጠል ጦርነት ማቆም አለብን”
- የኢትዮጵያን ልዕልናና አንድነት የሚገዳደር ነገር መፋለም ያለ የሚኖር ነው፤ ከዚያ በመለስ ደግሞ መነጋገር ያስፈለጋል።
- የትግራይ ህዝብ የጥይት ድምጽ አይስማ የተባለው በመንግስት በኩል ከጦርነቱ በፊት ነበር።
- “ጦርነቱ ሰሜን ሸዋ ደርሶ ከዚያ ሲቀለበስና እስረኞች ሲፈቱ ብዙዎች ተቀይመዋል። እኛ ግን ይህንን ያደረግነው ከሰላም ስለምናተርፍ ነው
- “በሰላም የሚጎዳ ኢትዮጵያዊ የለም አይባልም” ከጦርነቱ አትራፊ ነጋዴዎች አሉ።
- ሰላም ሲሆን ጦርነት፡ ጦርነት ሲሆን ሰላም የሚሉ “ግራ የሚያጋቡ” አሉ።
- “ብዙ ችግር አለብን፤ ነገር ግን መነጋገር፣ መደማመጥ፣ መልሶ መመርመርና መጨረስ” ያስፈልጋል
- ተነጋግረው የተስማሙት ሁለቱም ወገኖች ቃላቸውን መጠበቅ አለባቸው። “ተወያይተናል፣ ተስማምተናል፣ ፈርመናል። ለዚህ አበክረን መስራት አለብን”
- “ህገ መንግስቱ ከአሸባሪ አትደራደር አይልም፤ አታስታጥቅ ነው የሚለው”
ወልቃይትን በተመለከተ፡-
- ወልቃይትን በተመለከተ ብዙ ሴራዎች አሉ። እነዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ የለበትም።
- ወልቃይት ለትግራይ ወይም ለአማራ ይሁን የሚል አጀንዳ ፕሪቶሪያ ላይ አልተነሳም፤ ጉራጌ ክልል ይሁን አይሁን የሚለው እንዳልተነሳው ሁሉ።
- ህወሃት ከህገመንግስቱ በፊት በሃይል ወልቃይትን ወደትግራይ ጠቅልሏል። ያሁኑ መንግስት ተመሳሳይ ስህተት መስራት አይፈልግም።
- ወልቃይት የሁለቱም ህዝቦች ድልድይ ነው።
- መንግስት ውስጥ ስራቸውን በትክክል የማይሰሩ ግለሰቦች ቢኖሩም የሰላም ሂደቱ እንዳይሰናከል ጥንቃቄ እየተደረገ ነው።
- ብልጽግና ማለት ኢትዮጵያ እንዳልሆነው፣ አብን ማለት አማራ እንዳልሆነው፣ ህወሃትም የትግራይ ህዝብ ማለት አይደለም። ስለዚህ የትግራይን ህዝብ የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ማገዝ አለበት ለመልሶ ግንባታ።
- “ትግራይ ገብተን ያየነው ህዝቡ ሰላም፣ ውሃ፣ መብራት እንደሚፈልግ ነው”
- ህወሃት የአማራን ህዝብ ከወልቃይት ከዚህ በፊት ስላፈናቀለ ሪፈረንደም ቢደረግ አማራ ይጎዳል የሚሉ ወገኖች አሉ፣ አሁን ደግሞ በጦርነቱ የትግራይ ተወላጆች ስለተፈናቀሉ ትግራይ ትጎዳለች የሚሉ ወገኖችም አሉ።
በጦርነት የተጎዱ ቦታዎችን በተመለከተ፡-
- መደገፍ፡ እህል በማቅረብ፣ ምርት በመሰብሰብ በሌሎችም መደገፍ
- መገንባት፡ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት
- መመለስ፡ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቀያቸው መመለስ ላይ እየተሰራ ነው።
ኦነግ ሸኔን በተመለከተ፡-
- “በሽብር የሚገኝ ነጻነት፣ ዲሞክራሲ፣ ዘላቂ ጥቅም የለም”
- ሸኔ እንኳን ለመንግስት ለሚልኩትም ያስቸገረ የማይጨበጥ፣ ስርዓት የሌለው ቡድን ሆኗል
- ለኦሮሞ ቆምኩ ቢልም ኦሮሞና ኦሮሚያን እያደናቀፈ ይገኛል
- ሸኔን ጨምሮ ለማንም የታጠቀ ቡድን ያለን መርህ ተመሳሳይ ነው፤ በትጥቅ የሚመጣ መፍትሄ የለም፣ በንግግር መስማማት ይቻላል።
- መንግስት ሰፊ ስራ እየሰራ ቢሆንም ስራው ቀላል አይደለም
አዲስ አበባ እንዳይገቡ የተከለከሉ መንገደኞችን በተመለከተ፡-
- አዲስ አበባ መገደኞች እንዳይገቡ የሚከለከሉት የሽብር ጥቃቶችን ለመከላከል ነው
- የተከፈላቸውና ለሽብር ስራ የተሰማሩ ወጣቶች አሉ
- በዚህ ጉዳይ መጉላላት የሚደርስባቸው ዜጎች ቢኖሩም ለሃገር ሰላም ነው ተብሎ መታሰብ አለበት
ሙስናን በተመለከተ፡-
- ሙስና በጣም ተንሰራፍቷል፤ የተሰረቀን ገንዘብ ወደ ህጋዊ መስመር ማምጣት ይከብዳል
- “እንደማህበረሰብ ሁሉም ተቋማት ውስጥ ሌብነትን እየተለማመድን ነው”
- የፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቷል፣ “በቴሌግራም ቻናል ከፍተው ጉቦ የሚላላኩ ዳኞች አሉ”
- ይህን ለማጥራት እየተሰራ ነው፣ እንደተፈለገው ግን እየሄደ አይደለም
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መርሆች፡-
- ነጻነት፣ እኩልነትና ፍትሃዊነት
- ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ መፈለግ
- በርካታ ችግር ቢኖርም በጋራ ማሸነፍ (win-win situation)
ዲፕሎማሲን በተመለከተ፡-
- ባለፉት 3 ወራት ከጎረቤት ሃገራት ጋር አበረታች ለውጥ አለ፣ ሱዳንን ጨምሮ
- በአለማቀፍ መድረኮች ላይ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን ቆማለች፣ ከህወሃት ጋር በተደረገው የመጨረሻ ውጊያም ሱዳን አልተሳተፈችም
- በሰላም ስምምነቱ ላይ ለተሳተፉ ግለሰቦችና ተቋማት እንዲሁም ሃገሮች ኢትዮጵያ ታመሰግናለች
- ሁሉም ዜጋ ለሃገሩ ዲፕሎማት መሆን አለበት፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጭምር
- የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ባሉበት የውጪ ሃገራት በመንግስት ስራዎች፣ ፓርላማዎች ውስጥ ተመራጭ በመሆን ሃገራቸውን መደገፍ አለባቸው
- በ50ዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙት ከ50 ሺ በላይ ምሁራን በጥናታዊ ስራዎች በዲጂታል አውድ ውስጥ ውጤት ማምጣት አለባቸው
- “የኢትዮጵያ ታክሲ ማህበራት መንግስት ባይደግፋቸውም መንግስትንና ሃገራቸውን ለመደገፍ ያደረጉትን ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት ያመሰግናል”
ብሄራዊ ምክክርን በተመለከተ፡-
- የምክክር ኮሚቴው አባላት የሚሳካላቸው የህዝብ ድጋፍ ሲያገኙ ነው
- መንግስት ሙሉ ድጋፍ አለው
- ምክክሩ በአግባቡ ከሄደ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው፤ 70-80% ችግራችንን ሊያቃልል ይችላል