መጋቢት 21 ፣ 2014

ከትላንት ምሽት ጀምሮ የተዘጋው የኢትዮ-ጅቡቲ የንግድ መስመር መከፈቱ ተሰማ

City: Adamaዜና

መንገዱ የተዘጋው በኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ገቢ ንግድ መስመር ላይ በምትገኘው “አውራ ጎዳና” በተሰኘች አነስተኛ መንደር አካባቢ በተነሳ ግጭት ነው። በግጭቱ ምክንያት ዋና ዋና መንገዶች በመዘጋታቸው አሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም ነበር።

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

Addis Zeybe is a Digital News Media.

ከትላንት ምሽት ጀምሮ የተዘጋው የኢትዮ-ጅቡቲ የንግድ መስመር መከፈቱ ተሰማ
Camera Icon

ፎቶ፡ Google maps

ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተዘግቶ የነበረው ኢትዮ ጅቡቲ መስመር መከፈቱ ተሰምቷል። ከመተሀራ ወጣ ብሎ የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ስር በሚገኘውና “አውራ ጎዳና” ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥዋት 4፡00 ድረስ ተዘግቶ ቆይቷል።

መንገዱ የተዘጋው በኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ገቢ ንግድ መስመር ላይ በምትገኘው “አውራ ጎዳና” በተሰኘች አነስተኛ መንደር አካባቢ በተነሳ ግጭት ነው። በግጭቱ ምክንያት ዋና ዋና መንገዶች በመዘጋታቸው አሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም ነበር።

"አውራ ጎዳና" በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ስር የምትገኝ ሲሆን ከቀናት በፊት ሁለት አሽከርካሪዎች እንደተገደሉ ምንጮቹ ገልጸዋል። ብዙዎቹ አሽከርካሪዎች ሁኔታውን በመፍራት ወደ መተሐራ እና አዳማ ከተሞች ከነጭነታቸው እንደተመለሱ ሰምተናል።

አዲስ ዘይቤ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ እና ደህንነት ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ ከአዲስ ዘይቤ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ በስራ ጉዳይ ባህርዳር ከተማ መሆናቸውን ገለጸው የትናንቱ ግጭት ዛሬ መረጋጋቱን የነገሩን ሲሆን በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለጊዜው መረጃ የለኝም ብለዋል።

ትላንት ከሰዓት በኋላ ወደ ነዋሪዎች በድንገት ተኩስ ተከፍቶ ለሰዓታት ከተሰማ የተኩስ ድምጽ በኋላ መንገዶች ተዘግተው ቢቆዩም በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ ደርሰው ጉዳዩን በማረጋጋት መንገዱ እንዲከፈት ተደርጓል ተብሏል። በተኩስ ሩምታው በሰዎች ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን ለጊዜው አልታወቀም።