በያዝነው ዓመት መጀመሪያ የተመሰረተው ሂጅራ ባንክ 3ኛውን ‹‹አልቀሩፍ›› (ቅርንጫፍ) በባህርዳር ከተማ በይፋ ስራ አስጀምሯል። ባንኩ ዛሬ በይፋ ስራ ሲጀምር በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ብርሃን ንጉሤ በሀገሪቱ ብሎም በከተማው የሚታየውን የኢንቨስትመንት ክፍተት ለመሙላት "ሂጅራ ባንክ" አልፋሩቅ ቅርንጫፍ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀው ከተማ አሰተዳደሩ ከባንኩ ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በስነ-ስዓርቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሀሰን ሙሐመድ ባንኩ በመከፈቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብም አገልገሎቱን በመጠቀም የባንኩን እድገት እንዲያፋጥንም ጥሪ አቅርበዋል።
ሂጅራ ባንክ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተመሰረቱ በኋላ የምስረታ ካፒታላቸውን ወደ አምስት ቢሊየን ብር አንዲያሳድጉ የጊዜ ገደብ ከተቀመጠላቸው ባንኮች አንዱ ነው።የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ከባንኩ ጋር ትርፍና ኪሳራ የመጋራት ስርዓት እንጅ የወለድ ስርዓት አይከተለም ብለዋል። "ሸሪአን" መሰረት ያደረገ መሆኑ፣ በሸረአ በተፈቀዱ የስራ ዘርፎች ብቻ የሚሳተፍ መሆኑ፣ በአጋርነት መስራት መሰራታዊ ተግባሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለፕሮጀክቶች አዋጭነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑ፣ በብር አስቀማጩ እና በባንኩ መካካል ስጋት የመጋራት አሰራርን የሚከትል መሆኑ እና "ዘካን" ሰብስቦ ለሚመለከታቸው መስጠት አንዱ ተግባሩ መሆኑ የባንክን አገልግሎቶች ከሌሎች ባንኮች የሚለያቸው ነገሮች መሆናቸውን አብራርተዋል።
ባሳለፍነው ዓመት በኢትዮጵያ የሚገኙ ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት በሚሰጡ አሰራ ሁለት ባንክች 1.4 ትሪሊዮን ብር የባንክ ዝውውር ነበራቸው። ከዚህም ወስጥ በአንድ መስኮት የሚሰጡት ወለድ አልባ አገልግሎቶች ድርሻ 1.4 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው። የቀረበው አሃዝ 7 በመቶ እንደማለት ሲሆን እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን የሂጅራ ባንክ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
ባንኩ ከአሰር ሽህ በላይ በሆኑ ባለ አክዮኖች የተመሰረተ ሲሆን ከ260 በላይ ሰራተኞች እና ከሰባ ሁለት ሸህ ባላይ ደንበኞች አሉት።
ሂጅራ ባንክ ባህርዳር ከተማ በዛሬው እለት ያስመረቀውን ጨምሮ በአማራ ክልል አራት ቅርጫፍች አሉት።