ኅዳር 24 ፣ 2014

ስጋት የፈጠረውን የቦሌ አትላስ ድልድይ ለማደስ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተባለ

City: Addis Ababaዜናወቅታዊ ጉዳዮች

በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ቦሌ አትላስ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው ድልድይ የመፍረስ ስጋት ላይ ነው፡፡

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

ስጋት የፈጠረውን የቦሌ አትላስ ድልድይ ለማደስ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ቦሌ አትላስ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው ድልድይ የመፍረስ ስጋት እንዳንዣበበት በመገንዘብ አዲስ ዘይቤ ስለጉዳዩ ያነጋገረቻቸው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን ቢሮው ስለጉዳዩ መረጃ እንዳለው እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ እድሳቱን ለማከናወን ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገለፁ።

ምክትል ዳይሬክተሩ "የባለስልጣን መስርያ ቤቱ ቡድን ቦታውን ተመልክቶ እድሳቱ የሚከናወንበት መንገዶች ላይ ጥናት እያደረገ ነው፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥም እድሳቱ ይጀመራል" ያሉ ሲሆን እድሳቱን ለማከናወን ድልድዩ አገልግሎቱን ያቋርጣል ወይስ በስራ ላይ ሆኖ መካሄድ ይችላል በሚለው ላይ ገና ውሳኔ አለመተላለፉን አስረድተዋል።

ድልድዩ ላይ የደረሰዉ ጉዳት አነስተኛ መሆኑን የገለጹት ሀላፊዉ አሁን ላይ ድልድዩ አገልግሎት መስጠቱ የሚያሰጋ ነገር የለዉም ብለዋል።አክለውም የድልድዩ ጉዳት የተፈጠረው ለረዥም ጊዜ አገልግሎት ከመስጠት አኳያ መሆኑን በመጥቀስ በአሰራር ጥራት ጉድለት የተከሰተ አለመሆኑን አመላክተዋል።

የቦሌ አትላስ ድልድይ ከተለያዩ ሰፈሮች ጋር የሚያዋስን አይነተኛ ቦታ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ግለሰብ የድልድዩን የመፍረስ ስጋት የሚያሳይ ፎቶ  በፌስቡክ ግሩፕ ማጋራቱን ተከትሎ የተለያዩ ሰዎች ድልድዩ አደጋ ሳያደርስ በፍጥነት እንዲታደስ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ መልዕክቶችን በማጋራት ላይ ይገኛሉ።

አስተያየት