መጋቢት 18 ፣ 2014

የደሴ እና የባህርዳር ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ አምራች ማእከላት ከእቅድ በላይ ማምረታቸውን ተናገሩ

City: Bahir Darዜና

የባህር ዳር አካል ተሃድሶ ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት 1,847 ጥንድ ክራንች ያመረተ ሲሆን፤ ከያዝነው ዓመት ስድስት ወራት ጋር ሲነፃፀር የእቅድን 224.7 በመቶ አሳክቷል።

Avatar: Abinet Bihonegn
አብነት ቢሆነኝ

አብነት ቢሆነኝ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ትምህርት ምሩቅ ሲሆን። ዜና እና የተለያዩ ዘገባዎች የመፃፍ ልምድ አለው። አሁን በአዲስ ዘይቤ የባህር ዳር ሪፖርተር ነው

የደሴ እና የባህርዳር ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ አምራች ማእከላት ከእቅድ በላይ ማምረታቸውን ተናገሩ
Camera Icon

ፎቶ፡Istock

ባለፉት 6 ወራት ብቻ 2ሺህ 444 ጥንድ ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ መስጫ (ክራንች) የማምረት እቅድ የነበረው የባህርዳር ተሃድሶ ማዕከል የእቅዱን 327.8 በመቶ ማሳካቱን አስታውቋል። ማእከሉ የ6 ወር አፈጻጸሙን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንደተባለው የ6 ወራቱ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ40 በመቶ ብልጫ አለው። የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም ካለፉት ሁለት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም በእጥፍ ማደጉ ተነግሯል። ሪፖርቱ እንደ ክራንች፣ ዊልቸር፣ የዓይነ ስውራን በትር (ኬን) ያሉ ምርቶቹን በጦርነቱ ለተጎዱ የፌደራልና የክልል ጸጥታ አካላት ማቅረቡን የተቋሙ መረጃ ያሳያል።

የባህር ዳር አካል ተሃድሶ ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት 1,847 ጥንድ ክራንች ያመረተ ሲሆን፤ ከያዝነው ዓመት ስድስት ወራት ጋር ሲነፃፀር የእቅድን 224.7 በመቶ አሳክቷል። በሌላ በኩል ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 117.8℅ በመቶ ብልጫ እንደሚያሳይ የተቋሙ ሪፖርት ያሳያል።

በተመሳሳይ የደሴ አካል ተሃድሶ ማዕከል በክልሉ በምስራቅ አማራ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ሲሆን በ2013 በጀት ዓመት 1,829 ጥንድ ክራንች አምርቷል። ይህም ከ2012 ከተመረተው 1,683 ጥንድ ክራንች ጋር ሲነፃፀር ብልጫ አለው።

የባህር ዳር እና ደሴ የአካል ተሃድሶ ማዕከላት በጦርነቱ ምክንያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የፀጥታ አካላት ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፎች የማምረትት ኃለፊነታቸውን በመወጣታቸው በሀገርአቀፍ ደረጃ በጦርነቱ ወቅት ላበረከቱት አስተዋፆ የጤና ተቋማት ዕውቅና ሲሰጥ እውቅና አግንተዋል።

ወ/ሮ ያለምወርቅ ይታየው የባህር ዳር አካል ተሃድሶ ማዕከል ስራ አስኪያጅ ለአፈፃፀሙ ማድግ  ምክንያቶቸን አብራርተዋል። አንደ ስራአስኪያጇ ማብራሪያ "በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት ምክንያት ፍላጎቱ በማደጉ ነው" ይላሉ። በዚህም ማዕከላቱ በክልሉ "በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የፌድራል እና የከልል የፀጥታ አካላት ማሰራጨት ተችሏል" ማዕከሉ ጉዳት የደሰሰባቸው የፀጥታ አካላት ተኝተው የሚታከሙባቸው የህክምና ተቋማት ድረስ በመገኘት ሙያዊ ድጋፍን ጨምሮ ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ ምርቱን እንዳሰራጨ ስራ አስኪያጇ ገልፀዋል።

እንደ ማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ገለፃ ማዕከሉ ለችግሩ ትኩረት ሰጥቶ በብዛት በማምረት ማሰራጨት መቻሉን ገልፀው። መደበኛ የህክምና ተቋማት የክራች እና ሌሎች የሰው ስራሽ አካል ድጋፍ ግብአቶች ከፍተኛ እጥረት እንደነበረባቸው አስታውሰዋል።

እንደ የዓለምወርቅ ይታየው ማብራሪያ ማዕከሉ ይህንን ኃላፊነት የተወጣው ለመደበኛ ስራ በተመደበለት በጀት በመሆኑን አሁን የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ በደሴ ከተማ የሚገኘው ማዕከል ለምስራቅ አማራ እና በከፊል ለአፋር ከልል የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ የሚያደርስ ማዕከል ነው። አንደ ሥራ አስኪያጁ አቶ አለልኝ ይመኙ ማብራሪያ በበጦርነቱ ወቅት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው በምሰራቅ አማራ የሚገኙ የፀጥታ አካላት አገልግሎት መሰጠታቸውን አስታውሰው።

የደሴ አካል ተሃድሶ ማዕከል በጦርነቱ ምክንያት ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ ቢወድምበትም በአሁኑ ጊዜ ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ባገኘው ድጋፍ ወድስራ መግባቱን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

ማዕከላቱ ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች መካከል በራሳቸው ጥረት ተሸከርካሪ ወንበር (ዊልቸር) በማምረት እና ከረጂ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የዓይነ ስውራን ብትር ማምረትና ማሰራጨት፣ የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት እና የዞረ እግር (ክልብ ፉት) አገልግሎቶች መስጠት ይገኙበታል።

ማዕከላቱ ምርታቸውን ወደ ተቋሙ መምጣት ለማይችሉ የሌሎች ክልሎች ነዋሪዎች ለማዳረስ "አውት ሪች" የሚባል ፕሮግራም ነድፈው ወደ አካል ጉዳተኞቹ በመሄድ እርዳታ እንደሚያደርጉም ሰምተናል።