መጋቢት 2 ፣ 2014

በያዝነው ሳምንት ብቻ 35ሺህ የትግራይ ተፈናቃዮች ቆቦ ከተማ መግባታቸው ተነገረ

City: Dessieዜና

ተፈናቃዮቹ ወደ አማራ ክልል ለመፈናቀል ያስገደዳቸውን ምክንያት ሲጠየቁ የሰላም ማጣት፣ የምርት እጥረት፣ መንግሥት አልባነት፣ ስርአተ-አልበኝነት የአደጋ ስጋትና ረሀብ በማስከተላቸው እንደሆነ መግለጻቸውን ኃላፊው አንስተዋል።

Avatar:  Idris Abdu
እድሪስ አብዱ

እድሪስ አብዱ በደሴ የሚገኝ የአዲስ ዘይቤ ዘጋቢ ነው።

በያዝነው ሳምንት ብቻ 35ሺህ የትግራይ ተፈናቃዮች ቆቦ ከተማ መግባታቸው ተነገረ

ወደ ቆቦ ከተማ የሚገቡ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ እንደሚገኝ የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታወቀ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ዓለሙ ይመር ለአዲስ ዘይቤ እንደተናገሩት በዚህ ሳምንት ብቻ ከ35 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ከመላው ትግራይ ወደ አማራ ክልል ቆቦ ከተማ ገብተዋል።  

ከትግራይ ክልል ወደ አማራ ክልል በመግባት ላይ የሚገኙት የተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው ከትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እና የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉትን ጨምሮ ቁጥራቸው ከ63ሺህ 723 በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በአማራ ክልል ስር ከሚገኙ የራያ ቆቦ 8 ቀበሌዎች፣ ከአላማጣ ከተማ እና ከአላማጣ ዙሪያ ከተሞች፣ ከባላ አካባቢ የተፈናቀሉት ሰዎች ቆቦ ከተማ በሚገኙ 4 ት/ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እንደሚኙ ኃላፊው አስታውቀዋል።

አቶ ዓለሙ በተጨማሪም “የአካባቢው ነዋሪ ተፈናቃዮች በመቀበል እያስተናገደ ይገኛል። የፀጥታ ኃይሉም ከትግራይ ክልል የሚመጡ ሰዎች ላይ ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር በማድረግ ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ ተደርጓል” ብለዋል።

ተፈናቃዮቹ ወደ አማራ ክልል ለመፈናቀል ያስገደዳቸውን ምክንያት ሲጠየቁ የሰላም ማጣት፣ የምርት እጥረት፣ መንግሥት አልባነት፣ ስርአተ-አልበኝነት የአደጋ ስጋትና ረሀብ በማስከተላቸው እንደሆነ መግለጻቸውን ኃላፊው አንስተዋል።

የዞኑ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮም ከአማራ ክልል እና ከፌደራል አደጋ መከላከልና ዝገጁነት ቢሮዎች ጋር በመነጋገር ለተፈናቃዮች የምግብና አልባሳት አቅርቦት እያደረሱ እንደሚገኙ፣ ተፈናቃዮቹ በቀጣዮቹ ሳምንታት ከቆቦ ከተማ በዞኑ ድሬ ሮቃ እና ጃራ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች እየተገነቡ ወደሚገኙ መጠለያ ካምፖች ለማዛወር ሥራዎች መጀመራቸውን ገልፀዋል።

አስተያየት