ግንቦት 18 ፣ 2014

ያለ ቅድመ ሁኔታ ሱቃችን እየታሸገብን እና የዳስ ጥላችን እየተነሳብን ነዉ" በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች

City: Hawassaወቅታዊ ጉዳዮችንግድ

በሐዋሳ ከተማ በተለያዩ የስራ መስክ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሱቃችን እየታሸገብን እና ለማስታወቂያ እና ለጥላ የተተከሉ ዳሶች እየተነሱብን ነዉ ሲሉ ተነግረዋል።

Avatar: Eyasu Zekariyas
ኢያሱ ዘካርያስ

ኢያሱ ዘካርያስ በሀዋሳ የሚገኝ የአዲስ ዘይቤ ዘጋቢ ነው።

ያለ ቅድመ ሁኔታ ሱቃችን እየታሸገብን እና የዳስ ጥላችን እየተነሳብን ነዉ" በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች
Camera Icon

ፎቶ፡ አላዛር ሀይሉ

ለአዲስ ዘይቤ ቅሬታቸዉን ያቀረብት በመናኸሪያ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የህፃናት የልብስ ነጋዴ የሆኑት አቶ የሱፉ እንድሪስ ለሁለት ዓመታት በስራዉ ላይ እንደቆዩ በማስታወስ ዛሬ ምን እንደገጠማቸዉ ነግረዉናል  "አራት ሰዎች ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ መጥተዉ በህገወጥ የተተከለ እና ከፕላን ዉጪ  ነዉ በሚል ግርግዳ ላይ የተለጠፈዉን ታፔላ ተነስቷል"፤ በተጨማሪ የልብስ መስቀያዉ አሻንጉሊት በተመሳሳይ ከቦታዉ እንዲነሳ ተደርጎብኛል" ።

በዛሬው ዕለት ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የልብስ ሱቆች ፣ የምግብ ቤቶች ፣ ሱፐር ማርኬቶች ፣ እንዲሁም መደበኛ ሱቆች ከከተማ አስተዳደር በመጣ ትዕዛዝ ነዉ በሚል ከይዞታ ዉጪ የሆኑት እና በተገቢው መንገድ ግብር ባልከፈሉት ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ከንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል። 

"ህጋዊ ግብር ከፋይ"  ነኝ በዚህ ስራ ከሶስት ዓመት በላይ ቆይቻለሁ ነገር ግን ዛሬ የተፈጠረዉ ፍፅሞ ያልጠበኩት በመሆኑ አስደንግጦኛል የሚሉት ደግሞ ወ/ሮ እቴነሽ መላኩ ሲሆኑ አነስተኛ ግሮሰሪ እንዳላቸዉ እና ለዛዉ የቤት ኪራይ 3 ሺህ ብር በየወሩ እንደሚከፍሉ ተናግረዋል። ወ/ሮ እቴነሽ እንደሚሉት የምሰራበት ቤት ጠባብ በመሆኗ በበረንዳ ላይ ዳስ ጥዬ ነዉ ደንበኞችን የማስተናግደዉ ነገር ግን አሁን ላይ ተነስቷል፤ በዚህ ከቀጠለ ደግሞ ለአራት ልጆቼ እና ለእራሴ መሆን አልችልም " በማለት ጉዳዩን የሚመለከተዉ አካል መፍትሔ እንዲያበጅለት ጠይቀዋል። 

በሐዋሳ ከተማ "በስምንቱም ክፍለከተማ በሚገኙ ህገወጥ ተብለዉ የተለዩ እና ከይዞታ ዉጪ የተገነብ" እያንዳንዳቸዉ ንብረት እንዲፈርስ እየተደረገ መሆኑን እንዲሁም "ለግሪነሪ (Green Area) የተቀመጠውን ህግ በጣሱት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነዉ " የሚሉት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት በላይነሽ  ገዳ ነገር ግን "ከህግ አግባብ ዉጪ የተደረገ ምንም አይነት አሰራር የለም"  በማለት ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል። 

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር "ከይዞታ ዉጪ ያለዉን አረንጓዴ ስፍራ (Green Area) የገነቡትን ግንባታ እንዲያነሱ ስለመጠየቅ " በሚል ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በሁሉም ክፍለከተማዎች  ላይ በንግድ ስራ ለተሰማሩት የይዞታ ባለቤቶች  በተፃፈ ደብዳቤ ማሳወቁን ተመልክተናል።

አስተያየት