ሚያዝያ 6 ፣ 2015

ህውሓት ለኮረምና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መመደቡ ታወቀ

City: Mekelleወቅታዊ ጉዳዮች

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአካባቢዎቹ አመራር የመደበ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊት ከስፍራው እስከሚወጣ ስራ አይጀምሩም

Avatar: Getahun Asnake
ጌታሁን አስናቀ

ጌታሁን አስናቀ በጎንደር የሚገኝ የአዲስ ዘይቤ ዘጋቢ ነው።

መሰረት ፀጋይ

መሰረት ፀጋይ በጋዜጠኝነት ስራ ልምድ ያላት ሲሆን የአዲስ ዘይቤ የመቀሌ ከተማ ዘጋቢ ናት።

ህውሓት ለኮረምና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መመደቡ ታወቀ

የኮረም እና አላማጣ አካባቢዎችን ለማስተዳደር የህወሓት ቡድን ለአካባቢዎቹ አመራር መድቦ የመከላከያ ሠራዊትን ከአካባቢው መውጣት እየተጠባበቀ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ከምንጮቿ አረጋግጣለች።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎች እና ኢ-መደበኛ ታጣቂዎችን ወደ መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል እና የከተማ ፖሊስ ሆነው እንዲቀላቀሉ ባቀረበው ጥሪ ሳቢያ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላትና ፋኖዎች ጥሪውን ተቃዉመው መቆየታቸው ይታወሳል። ከዚህም ባለፈ “ትጥቅ አንፈታም” ባሉ ታጣቂዎች እና መከላከያ ሰራዊት መካከል ተኩስ ተከፍቶ ነበር። 

ይሁን እንጂ በአላማጣ እና ኮረም ከተማዎች እና በዙሪያው ሰፍረው የቆዩት በርካታ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የፋኖ ታጣቂዎች ከትጥቅ ፍቱ ጥሪ ጋር ተያይዞ ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ህውሓት ለአካባቢዎቹ አመራሮችን እንደመደበ አዲስ ዘይቤ ከትግራይ ክልል ህጋዊ ታጣቂ አባላት አረጋግጣለች።

በትግራይ ክልል የሚገኘው የክልሉ ልዩ ኃይል አባል ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፀው ህውሃት አመራሮችን መድቦ የጨረሰ ቢሆንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው ስላልወጡ አመራሮችን መላክ አልተቻለም ብሏል። ለአካባቢዎቹ የተመደቡት አመራሮች በአሁኑ ሰዓት መቀሌ ከተማ እንደሚገኙም ታውቋል። 

ከአዲስ ዘይቤ ጋር ቆይታ ያደረጉ የአላማጣና የኮረም ነዋሪዎች ፋኖና ልዩ ኃይል ከአካባቢው ሲወጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የተተካ ቢሆንም ስጋት ውስጥ ከቶናል ሲሉ ይገልፃሉ። ለሁለት ዓመታት በጦርነት ቀጠና የቆዩት አላማጣ እና አካባቢው አሁንም ድጋሚ ጦርነት እንዳይነሳ ያሰጋናል ሲሉም ተናግረዋል።የኮረም እና አላማጣ አካባቢዎችን ለማስተዳደር የህወሓት ቡድን ለአካባቢዎቹ አመራር መድቦ የመከላከያ ሠራዊትን ከአካባቢው መውጣት እየተጠባበቀ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ከምንጮቿ አረጋግጣለች።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎች እና ኢ-መደበኛ ታጣቂዎችን ወደ መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል እና የከተማ ፖሊስ ሆነው እንዲቀላቀሉ ባቀረበው ጥሪ ሳቢያ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላትና ፋኖዎች ጥሪውን ተቃዉመው መቆየታቸው ይታወሳል። ከዚህም ባለፈ “ትጥቅ አንፈታም” ባሉ ታጣቂዎች እና መከላከያ ሰራዊት መካከል ተኩስ ተከፍቶ ነበር። 

ይሁን እንጂ በአላማጣ እና ኮረም ከተማዎች እና በዙሪያው ሰፍረው የቆዩት በርካታ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የፋኖ ታጣቂዎች ከትጥቅ ፍቱ ጥሪ ጋር ተያይዞ ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ህውሓት ለአካባቢዎቹ አመራሮችን እንደመደበ አዲስ ዘይቤ ከትግራይ ክልል ህጋዊ ታጣቂ አባላት አረጋግጣለች።

በትግራይ ክልል የሚገኘው የክልሉ ልዩ ኃይል አባል ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፀው ህውሃት አመራሮችን መድቦ የጨረሰ ቢሆንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው ስላልወጡ አመራሮችን መላክ አልተቻለም ብሏል። ለአካባቢዎቹ የተመደቡት አመራሮች በአሁኑ ሰዓት መቀሌ ከተማ እንደሚገኙም ታውቋል። 

ከአዲስ ዘይቤ ጋር ቆይታ ያደረጉ የአላማጣና የኮረም ነዋሪዎች ፋኖና ልዩ ኃይል ከአካባቢው ሲወጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የተተካ ቢሆንም ስጋት ውስጥ ከቶናል ሲሉ ይገልፃሉ። ለሁለት ዓመታት በጦርነት ቀጠና የቆዩት አላማጣ እና አካባቢው አሁንም ድጋሚ ጦርነት እንዳይነሳ ያሰጋናል ሲሉም ተናግረዋል።

አስተያየት