መንደርደሪያ
ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ፓርቲያቸው የሚመራው የኢትዮጲያ መንግስት በዜጎችላይ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽም መኖሩን አምነዋል። የፌደራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መንግስት ከወራት ምርምራ በኃላ ሰፊየሰብዓዊ መብት ጥሰት (በተለይ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ማሰቃየት) እና ከባድ የሙስና ወንጀሎች መፈጸማቸውን እንደደረሰበትተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ ዜጎች ፍትህ ስለሚያገኙበት አጋጣሚ በየአቅጣጫው ውይይት ሲደረግ ከራርሟል። በሰብዓዊ መብት ጥሰትየተጠረጠሩ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የደኅንነት እና የፖሊስ አባላትም ሲታሰሩ እየተሰማ ነው። ሰፊ እናከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም የዜጎች ፍትህ የማግኛ አካሄዶች በሁለት አቅጣጫ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው አጥፊውንበመቅጣት እና ተበዳዮችንም በመካስ፤ ተበዳዮቹ ፍትህን በማግኘታቸው የሚረኩበት (Retributive Justice) ሲሆንሁለተኛው ደግሞ ተበዳዮች በአደባባይ ስለ በደላቸው የሚናገሩበት እና በዳዩም ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ የሚጠይቅበት፤ ተበዳዮቹምየሚካሱበት እና ከበዳያቸውም ጋር ይቅር የሚባባሉበት አካሄድ (Restorative Justice) ነው።
ሀገራት የፖለቲካ ለውጥ በሚኖርበት ወቅት ወይም ከውስጥ፣ በእርስ በርስ ግጭት ከተላቀቁ በኃላ የሁለተኛውንየፍትህ አካሔድ ለመምረጥ የሚገደዱባቸው የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። በፖለቲካ ለውጥ ጊዜ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተሳተፉትየቀድሞዎቹ የመንግስት ኃላፊዎች ከፖለቲካው ስልጣን ውስጥ ተጠቃለው ስለማይወጡ፤ ወንጀሎችን ለመደበቅ እና ማስረጃዎችንምለማጥፋት ምቹ ሁኔታ ላይ ይሆናሉ። በዚህም ምክንያት አጥፊዎቹን በወንጀል የፍርድ አካሄድ መርምሮ መቅጣት አስቸጋሪ ይሆናል።እንዲሁም በመንግስት ስር የሚፈጠሩ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በየደረጃው ብዙ ሰዎችን ስለሚያካትተቱ፣ ድርጊቶቹም ሰፊናውስብስብ ስለሚሆኑ በፖለቲካ ለውጥ ወይም ድህረ-ግጭት ጊዜ የሚኖሩ የወንጀል የፍትህ ስርዓቶች ጉዳዩን ለመመርመር በቂ ተቋማዊብቃት አይኖራቸውም። የሚወስደው ጊዜ እና የሚወጣው ወጪም ከፖለቲካ ለውጥ በኃላ ለሚኖር አስተዳደር ቀላል አይሆንም። ከዚህምባሻገር የወንጀል ፍትህ ስርዓቶች በግለሰቦች ላይ ብቻ የተገደቡ ስለሚሆኑ በሰብዓዊ መብት እና ግጭት ምክንያት የተፈጠሩ ማኀበረሰባዊቁርሾዎችን ለማስታረቅ አይቻለውም። እንደውም ከዚህ በተቃራኒው አሁን በሀገራችን እንደምንሰማው ፍትህ ለተመረጡ ሰዎች ብቻእየተሰጠች (Selective justice) እንደሆነ እና ለፖለቲካ መጠቀሚያም እየዋለች (Political prosecution)እንደሆነ ሊቆጠር እና በሕብረሰተቡ መካከል ያሉ ቆርሾዎችን ለማስፋት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች ቅጣትንመሰረት ያደረገ የወንጀል ተጠያቂነት ይልቅ ከሁለተኛው የፍትሕ አቅጣጫ ሒደት ጋር የሚገናኘው እውነት እና እርቅ (Truthand Reconciliation) ተመራጭ ይሆናል፡፡
እውነት - ወደ እርቅ መዳረሻ
ተበዳይ ለበደሉ ይቅርታ ለማድረግ የበዳዩን ማንነት ማወቅ አለበት። የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባ የሆነ ሰውፍ/ቤት ቢሄድ በደሉ መድረሱን ወይ በማስረጃ ማረጋገጥ አለበለዚያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን የፈጸመው አካል ማመን ይኖርበታል።በዳይ ከካደ እና ተበዳይ ማስረጃ ማምጣጥ ካቃተው ግን ጩኸቱ ሰሚ አልባ ሆኖ ይቀራል። ፍትህም ከእውነት ጋር ተቀብራ ትቀራለች።እውነት ከምንም በላይ በኩነት ውስጥ ባሉ ተሳታፊዎቹ ትገለጣለች። በዚህም ተበዳዩም የደረሰበትን፣ በዳዩም ያደረሰውን ጉዳትሲገልጹ መተማመን፣ ይቅር መባባል ይመጣል። ይሄ ሒደት በሁለቱ ግለሰቦች - በበዳይ እና ተበዳይ - መካከል ብቻ ሳይሆን በማኀበረሰብእና በመንግስት/ማኀበረሰብ መካከል እርቅ እንዲወርድ ምክንያት ይሆናል።
የእውነት አላማው በታሪክ የተፈጠሩ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በአደባባይ በማውጣጥ እና በመተማመን፤በበዳይ እና በተበዳይ መካከል ያለውን የተዛባ ግንኙነት ማከም፣ ወደ እርቅ ማምጣት ነው። ከዚህም ባሻገር እውነት መውጧቷለተባዳዩ (ለበዳዩም) ሰላም ይሰጣል። እውነትን በማውጣት እና እርቅ በመፍጠር ሁለቱ አካላት ወደ ሰላማዊ ግንኙነትየሚያመሩበትን፣ አንዱ ለሌላው ያለውን መጥፎ እይታም/አመለካከት ለማጥፋት ይቻላል። ወደ ፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን፣ የበቀልመንፈስንም ማስወገድ ይቻላል።
በተለያዩ ሀገራት እንደታየው ይህንን የእውነት እና የእርቅ ሒደቶች የሚመሩ ኮሚሲዮኖች ይመሰረታሉ። እነዚህየእውነት እና እርቅ ኮሚሲዮኖች በሀገሪቱ ርዕሰ-መንግስት ትእዛዝ ወይም በሕግ ሊፈጠሩ ይችላሉ። የጠ/ሚ ዐቢይ ካቢኔም “ለበርካታዓመታት በተለያዩ ማኀበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት በሕዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶች ለማከም እውነት እናፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅን ለማውረድ” በማሰብ “ብሔራዊ እርቀ-ሠላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ”ን በሕዳር 5 ቀን 2011ዓ.ም ላይ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል። ምክር ቤቱም የተለያዩ ነገሮች ላይ መጠነኛ ክርጅር ካደረገ በኃላ በአንድ"ተቃውሞ"፣ አንድ "ድምጸ ተአቅቦ" የኮሚሲዮኑን መመስረቻ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
ኢትዮጲያ የራሷን ታሪክ፣ ባህል እና የፖለቲካ ሁኔታ ያገናዘበ ኮሚሲዩን ማቋቋም እንዳለባት እሙን ቢሆንምየሌሎቹን ተሞክሮ ማየቱ አይከፋምና፤ በዚህ ጽሑፍ ላይ ከሌሎቹ አንጻር በኢትዮጲያ የእውነት እና እርቅ ሒደት ውስጥ ምን ምን ቢካተትበተሻላ ውጤታማ ይሆናል - ወደ ፍትህ፣ ማኅበረሰባዊ እርቅ እና የወደፊት ግጭቶችንም ወደ ማስቆም ይወስደናል - የሚለውንለማየት ይሞከራል።
ሀ. ቅቡልነት እና የማኀበረሰቡን እምነት
በመጀመሪያ ኮሚሲዮኑ በማኀበረሰቡ፣ በበዳይም ሆነ በተበዳይ እምነት የሚጣልበት መሆን አለበት። የማኀበረሰቡንፍላጎት እንወክላለን የሚሉ የፖለቲካ ሀይሎች እና የሲቪል ማኀበረሰብ አካላት በኮሚሲዮኑ ላይ እምነት ሊኖራቸው ያሻል። ይህንንማረጋገጥ የሚቻለው በዋነኛነት በአመሰራረቱ ሒደት ውስጥ በሚኖረው አካሄድ ነው። የኮሚሲዮኑ አባላት የሚሆኑ ሰዎች በጥንቃቄመመረጥ አለባቸው። ይሄም ማለት አባላቱ በተቻለ መጠን መሃል ሰፋሪ እና ገለልተኛ መሆናቸው የሚታመንባቸው እና በማኀበረሰቡምዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል። በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እና ታማኝነት ያላቸው፤ እንደ የሀይማኖት አባቶች፣የባህል ሽማግሌዎች እና የሰብዓዊመብት ተማጓቾች አይነት ሰዎች ማካተቱም የኮሚሲዮኑን ቅቡልነት ያሳድገዋል። እንደ ኢትዮጲያ ባለ ፖለቲካዋ በተለያዩ የቡድንምንነቶች በተሸበበች ሀገር አባላቱ ከሁሉንም ጎራ ያሳተፈ መሆኑ የተሻለ ተአማኒነት እንዲያገኝ ምክንያት ይሆናል። የአዋጁመግለጫ በሚል በወጣው የባለ 2 ገጽ ማብራሪያ የኮሚሲዮኑ አባላት "...በሁሉም ዜጎች ዘንድ ክብርና ተቀባይነት ያላቸውእና እስከ አሁን ስማቸው በየትኛውም ብሔር ወይም አካባቢ በመጥፎ የማይነሳ የተከበሩ ዜጎች..." እንደሚሆኑ ያስቀምጣል።
የኮሚሲዮኑ አባላት አሰያየምም ለሕዝቡ ግልጽና ሕዝቡም በምርጫው ውስጥ (እጩ በማቅረብ ወይም በመምረጥ)የሚሳተፍበትን አካሄድ ማመቻቸት ለኮሚሲዮኑ ቅቡልነት ወሳኝ ነው። እንደ አዋጁ አገላለጽ የኮሚሲዮኑ አባላት በጠቅላይ ሚንስትሩእጩነት በተወካዮች ምክር ቤት እንሚሰየሙ ይገልጻል። ነገር ግን አዋጁ በአባላቱ አመራረጥ ላይ ማኀበረሰቡ ስለሚሳተፍበት አጋጣሚምንም አይልም። ይህም ቢሆን የጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ እጩዎችን ወደ ተወካዎች ምክር ከማቅረቡ በፊት ሕዝቡን የሚያሳትፈበት እናስለ አባላቱ ሀሳብ የሚሰጥበትን አጋጣሚ ቢፈጥር ሕዝቡ ለኮሚሲዮኑ ባለቤትነት እንዲሰማውና በአግባቡም እንዲተባበር ምክንያትይሆናል።
ከዚህ ባሻገር የኮሚሲዮኑን ቅቡልነት ማረጋጋጥ የሚቻለው ኮሚሲዮኑ ስራውን በሚሰራበት ወቅት በሚኖረውገለልተኝነት ነው። ይሄገለልተኝነት በምርመራ ጊዜ በሚኖር ስራ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻን ሪፖርት በሚያዘጋጅበት እና በበጀት አመዳደብም ሊሆን ያሻዋል።በጀት በመንግስት ተቋም የሚመደብለትም ቢሆንም አጠቃቀሙ በኮሚሲዮኑ ውሳኔ ላይ ብቻ የተገደበ ሊሆን ይገባል። ይሄን በሚመለከትየአዋጁ "ኮሚሽኑ ስራውን በነጻነትና እና በገለልተኝት" እንደሚያከናውን ሰፋ ባለ አገላለጽ ያስቀምጣል።
ለ) የኮሚሲዮኑ ኃላፊነት
ስለኮሚሲዮኑ ኃላፊነት ስንናገር ምን ስራዎችንእንደሚሰራ እና የትኛዎቹን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንደሚያረጋገጥና እንደሚያጠና ማንሳት ይገባናል። ኮሚሲዮኑ የሚሰራቸውስራዎች እና ስልጣኑ በግልጽ መቀመጥ፣ ግን ደግሞ የኮሚሲዮኑን የስራ ነጻነት በማይሻማበት አካሄድ ሰፋ ባለ አገላለጽ መቀመጥይኖርባቸዋል። የኮሚሲዮኑ ስራዎች ዝርዝር እንደ ሰዎችን (በዳይ፣ ተበዳይ እና ምስክሮችን) ማነጋገር፣ ከመንግስት ተቋማትእርዳታ፣ መረጃ እና ማስረጃዎችን ጠይቆ የማግኘት፣ በተለያዩ ቦታዎች ተገኝቶ ጥናት ማድረግ፣ የመበርበር፣ ለምስክሮች ጥበቃየማሰጠት፣ ይቅርታ የማድረግ እና ቅጣት መጣልም የመሳሰሉ ሊሆኑ ይችላሉ። የትኞቹን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚመረምርም፣ተለይተው ባይገለጹም ከስፋት እና ክብደት አንጻር ተገልጾ ሊቀመጥ ያሻል።
አዋጁ በምንመለከትበት ጊዜ ኮሚሲዮኑ የሚሰራቸውስራዎች ኃላፊነቱን ባለገደበ በሰፊው ቢያስቀምጥም፤ የሚያጣራቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ግን በግልጽ አልተቀመጡም። ኮሚሲዮኑየማንኛውንም ሰው ቃል የመቀበል፣ የውይይት መድረኮችን የማዘጋጀት፣ ምርምራ ማድረግ፣ መረጃዎችን ከማንኛውም ተቋም የመቀበል፣ማንኛውንም ግለሰብ ጠርቶ የማነጋገር፣ እና ጉብኝቶችን የማድረግ የመሳሰሉ ስልጣኖች እንዷሉት ተገልጾአል። ነገር ግን ኮሚሲዮኑስራውን በሚሰራበት ጊዜ ለማይተባበሩም ሆነ ጣልቃ የሚገቡ ላይ የገንዘብም ይሁን የእስር ቅጣት የማስተላለፍ መብት አልተሰጠውም።ይህም ቢሆን ኮሚሲዮኑ "የፖሊስ እገዛ የማግኘት" መብት እንዳለው መደንገጉ መቅጣት ባይቻል እንኳን ግለሰቦችሆኑ ተቋማት ተገደው እንዲተባበሩ አማራጭ ይፈጥራል። የትኞቹን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ድርጊቶችእንዲሚያጣል በግልጽ አለመቀመጡ ግን በስልጣኑ ላይ ጥያቄዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
ለ. በቂ በጀት
የኮሚሲዮኑን ውጤታማነት ከሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የተቋሙ የበጀት አቅም ነው። ኮሚሲዎኑ ሰፊየምርመራ ስራ ሊኖርበት ይችላል። በውስጥ ባለሙያዎችን እና የተለያዩ ሰራተኞችን በመቅጠር የሚሰራቸው ጥናታዊ ስራዎችም ይኖራሉ።የተጎጂዎችን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን ቃል ለማድመጥም የሚኖሩ ወጪዎች ቀላል አይደሉም፡: ይህንንለመመዝገብና አጠናቆሮ ለማስቀመጥ ዳታ ቤዝ መገንባት ያሻል። የሰብዓዊ መብት፣ እና የስነ ልቦና ባለሙያዎችን ማሰራት ሊያስፈልግይችላል። ስለዚህ ኮሚሲዮኑ ያለበትን የስራ ብዛት ያገናዘበ በቂ በጀት መንግስት ሊመደብለት ይገባል።
ሐ. የመድረኩ ግልጽነት
ተበዳዎችም ሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች ቃላቸውን በሚሰጡበት ወቅት ሕዝቡእንዲከታተለው፣ ሚስጥራዊ እና በዝግ ቤት ውስጥ ሳይሆን ለሕዝቡ ክፍት በሆኑ አካሄድ ቢሆን በተሻለ ውጤታማ፣ ወደ እርቅምየሚያመጣ ይሆናል። የኮሚሲዎን እውነትን የማጥራት ስራ ከመጨረሻው ውጤቱ - ከድምዳሜው እና ምክረ ሃሳቡ ይልቅ ሒደቱ በማኀበረሰብመካከል እርቅን እንዲያመጣ ያግዛል። የተፈጠሩትን በደሎች በአደባባይ ሲገለጹ መታየታቸው የጎዳቱ ሰለባዎች የስነ ልቦና እርካታ፣እረፍት እንዲያገኙ ይረዳል። በተጨማሪም የሒደቱ ክፍት መሆን ሕብረተሰቡ የኮሚሲዮኑ ስራ ችግር እንዳለበት፣ አድሎአዊ እና"ማስረጃዎች የሚደበቁበት መድረክ ነው" ከሚል እምነት የጸዳ እንዲሆን ያደርጋል። ስለዚህ ከተቻለ ሒደቱ በሚዲያቀጥታ የሚተላለፍበት፣ ጋዜጠኞችም የሚሳተፉበት አጋጣሚ ቢኖር የተሻለ ነው ይመስለኛል። አዋጁ ኮሚሲዮኑ".. በሚስጥርም ሆነ ለሕዝብ ክፍት በሆነ ሁኔታ ቃለ መጠይቅ [የ]ማድረግ..." መብት ይሰጠዋል። በዚህምኮሚሲዮኑ የተጎጂዎችን ስለ ልቦና እና የማኀበረሰቡን ሞራል ሊጋፉ የሚችሉትን ብቻ በጥንቃቄ ለይቶ ሌላው ክፍት እንዲሆንመስራት፣ ሚስጠራዊነት ለተለየ ሁኔታ እንጂ መርኆው ክፍት መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል።
መ. የጊዜ ጉዳይ
ስለ እውነት እና እርቅ ሒደት ሲወራ ሌላው ወሳኝ ጉዳይ ጊዜ ነው። ጊዜ ሲባል ሒደቱ መች እንደሚጀምር፣ በምንያህል ጊዜ እንደሚጠናቅ ሲሆን ከመች እስከ መች የተፈጸሙ ጉዳዮች ኮሚሲዮኑ የሚያጠናም ይጨምራል። የእውነትና እርቅ ሒደትበተሻለ ውጤታማ የሚሆነው የፖለቲካ ለውጥ ከመጣ ወይም የነበረው የውስጥ ግጭት ከተወገደ በኃላ ወዲያውኑ ሲሆን እንደሆነይነገራል። ይሄም የተፈጠሩ ቆርሾዎች ወደ ቂም በቀል ሳይለወጡ፣ ማስረጃዎች ሳይጠፉ እና ማህበረሱም በእርቅ ሒደቱ ውስጥለመሳተፍ ያለው ተነሳሽነት ሳይጠፋ ሒደቱን ለማካሄድ ይጠቅማል። በዚህ ረገድ ጠ/ሚ ዐቢይ የሀገሪቷን ስልጣን ከተቆናጠጡ በኃላሀገሪቷን ከአምባገነን ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመውሰድ ቃል በገቡት መሰረት አሰተዳደራቸው የበፊት በደሎችን አጥርቶለማለፍ እና ወደፊትም የተቃና ግንኙነትን ለመፍጠር በማሰብ በወራት ውስጥ ኮሚሲዮኑን ለመመስረት ወስኗል። ይህም ቢሆን አሁንምኮሚሲዮኑ ከመቋቋሙ በፊት በአጭር ጊዜ ውስጥ የፖለቲካ ለውጡ ለጥቅማቸው አደጋ እንደሆነ የሚገነዘቡ አካላት እና ማኀበረሰቦችተፈጥረዋል። ይሄም ለተለያዩ ግጭቶች ምክንያት እየሆነ መጥቷል። የፖለቲካ ተሳትፎ፣ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ የግዛት ጥያቄ እናየመሳሰሉትን እንደምክንያት በመያዝ ለዓመታት ሲበስሉ የነበሩ የማኀበረሰብ ቁርሾችም ወደ ሰፊ ግጭቶች እየተለወጡ፣ ከሁለትሚሊዮን በላይ የውስጥ ተፈናቃዎች እንዲፈጠሩ ሆኗል። ከሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችላይ የተጀመሩ የወንጀል ማጣረት ሒደቶችም ኢ-ፍትሃዊ እና ፖለቲካዊ አድርገው የሚወሰዱ የማኀበረሰብ ክፍሎችም አሉ። በጠ/ሚዐቢይ አስተዳደር የሚመሰረት ኮሚሲዮን ውስጥ ለመሳተፍ ያለው እምነትም በተለያዩ የሕብረሰብ ክፍሎት ሊሸረሸሩ የሚችሉበት አጋጣሚቀላል የሚባል አይደለም። በዚህም ምክንያት ኮሚሲዮኑ መቋቋም ከነበረበት ጊዜ ዘግይቷል ማለት ይቻላል።
የኮሚሲዮኑ ስራ የሚሰጠው ጊዜ ስራውን ያገናዘበ፣ ቃላቸውን የሚሰማቸውን ሰዎች ለመጥራት እና ለመስማት፣ሌላ የምርመራ ስራዎች የሚያከናውንበትን እና የመጨረሻውን ሪፖርት ለማዘጋጀት የሚበቃውን ጊዜ በአግባቡ አጥንቶ ማስቀመጥ፣አስፈላጊ ሆኖም ሲገኝ ለአጭር ጊዜ ሊራዘም የሚችልበት አግባብ ማኖር ያሻል። በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅበትንጊዜ ማመቻቸት የእርቅ ሒደት በተሻለ ውጤታማ እንዲሆን ይረዳል። የኮሚሲዮኑ መመስረቻ አዋጅ የኮሚሲዮኑን የስራ ዘመን ሦስት ዓመታትእንዲሆን አስቀምጧል። ነገር ግን ይህ ጊዜ እንደአስፈላጊቱ እንደሚራዘም ቢገልጽም፣ እስከ ምን ያክል ጊዜ እንደሚራዘምአይገልጽም። ይሄም ሒደቱ እንዲጓተት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል፣ ሊራዘም የሚችልበትን የጊዜ መጠን ማስቀመጡ ጥሩ ነበር።
ኮሚሲዮኑ የሚመረምረው መች የተፈጠረውን ድርጊት መሆኑ በግልጽ መቀመጥ የሚኖርበት ሌላው ጉዳይ ነው። ነገርግን አዋጁ ይህንን ጉዳይ ሳያካትት ዘሎታል። እንደ አዋጁ አገላለጽ የእውነት እና እርቅ ኮሚሲዮኑን ማቋቋም ያስፈለገበት አንዱአላማ "ለበርካታ አመታት በተለያዩ ማኀበረሰባዊ እና ፓለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት በሕዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾስሜቶችን ለማከም፣ እውነትና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈላጊ" መሆኑን ይገልጻል። ነገር ግን አዋጁመች ላይ ስለተፈጠሩ "ማኀበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ግጭቶች" እንዲሚያወራ አይታወቅም። ይሄም የኮሚሲዮኑን ስራያለተገደበ፣ አወዛጋቢ እና የተዘርከረከ እንዲሆን ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ ባጠቃላይ አሁን ላይ በሕዝቡ ውስጥ ያለውን ቁርሾበአግባብ መርምሮ፣ ከባድ እና ሰፊ የመብት ጥሰትና ግጭት የተፈጠሩባቸውን ጊዜዎች አጥንቶ፣ ተፈጻሚነቱንም ሆነ ለእርቅ ያለውንጠቃሚነት ተገንዝቦ በሰከነ መንፈስ ጊዜውን አስቀምጦ መስራት ያሻል።
ሠ. ይቅርታ የማድረግ ስልጣን
በአንዳንድ ቦታዎች የተመሰረቱ የእውነት እና እርቅ ኮሚሲዮኖች ይቅርታ የማድረግ ስልጣን ሲኖራቸው፣ በሌላቦታዎች ላይ ደግሞ የላቸውም። ብዙ ጊዜ የኮሚሲዮኖቹ ስልጣን የተፈጠሩትን ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ማጣራት እና ይሄ ጥሰትየተፈጠረበትን የፖሊሲ እና የአሰራር ሒደት መመርመር፣ ከዛም ሪፖርት እና ምክረ-ሀሳብ ማቅረብ ነው። ስለዚህ ኮሚሲዮኑ ወይይቅርታ የሚያደርግበት አልያ ደግሞ የይቅርታ ምክረ-ሀሳብ የሚያቀርብበት ስልጣን ሊኖረው ይገባል።
ስለ ይቅርታ በሰፊው ተቀባይነት ያለው አካሄድ፤ ይቅርታ መደረግ ያለበት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥየተሳተፈው ግለሰብ ጥፋቱን፣ ስራውን በሙሉ ካመነ እና ይህንን ጥፋትም ያጠፋው በፖለቲካ ተገፋፍቶ እንጂ በግሉ ውሳኔ ካልሆነብቻ ነው። ከዚህ ባሻገር ትላልቅ እና የዓለም አቀፍ ወንጀሎችየሚባሉት፤ እንደ ጦር ወንጀል፣ ዘር ማጥፋት፣ ሰብዓዊነት ላይ በተጠና እና በሰፊው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ከተጠያቂነት ሊያመልጡእንደማይችሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸው ይመስላል፣ ከዚህ በፊት በተቋቋሙት ኮሚሲኒዎች ይህንኑ መረዳት ይቻላል።የኢትዮጲያ የወንጀል ሕግም የአለም አቀፍ ወንጀሎች ይቅርታ እንደማያሰጡ ይደነግጋል። ስለዚህ ይቅርታ የሚሰጠው መቼ ነው?፣ለየትኞቹስ ወንጀሎች ነው? የሚለው በግልጽ ታውቆ ወጥ በሆነ አሰራር ሊፈጸም ይገባዋል።
ነገር ግን በኢትዮጲያ የሚቋቋመው ኮሚሲዮን ይቅርታ የማድረግም ሆነየይቅርታ ምክረ-ሀሳብ የማቅረብ ስልጣን እንዳለሁ የተቀመጠ ነገር የለም። ኮሚሲዮኑ ይህን ስልጣን እንደለሌለው ይቅርታ በሌላአዋጅ እንደሚታይ በመግለጽ የውጪ ጉዳይ እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበሩ አቶ ተስፋዬ ዳባ አዋጁ በጸደቀበት ጊዜበግልጽ ተናግረዋል፡፡ ይህ በዳዮች በኮሚሲዮኑ ውስጥ ለመሳተፍ የሚኖራቸውን ተነሳሽነት ሊያሳንሰው እንደሚችል እሙን ነው።
ረ. ካሣ
የእውነት እና እርቅ አንደኛ አካሔድ ተበዳዮች የሚካሱበትን አጋጣሚ መፍጠር ነው። ካሳ በገንዘብ የሚተመንብቻ አይደለም። በገንዘብየሚተመኑ የሞራል እና ቁሳዊ ጉዳቶች ካሉ ተመጣጠኝ ካሳ ያስፈልጋቸዋል። ነገር ግን የፖለቲካ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ በሚደረግየእርቅ ሒደት ውስጥ ካሣ የሚከፍለው በሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ ከተሳተፈው ይልቅ፣ አዲሱ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው። የዚህምምክንያት በዳዩ ይቅርታ መባሉ፣ የመካስን ኃላፊነትም ይጨምራል ከሚል እሳቤ እና ለማስፈጸመም ከባድ ስለሚሆን ነው። በዚህምከፖለቲካ ለውጥ በኃላ ይሄንን የካሣ መጠን ሟሟላት የሚያስችል መዋለ ነዋይ ሊያጥር ይችላል። ለዚህም ግለሰቦች ከፈጸሙትበተጨማሪ ተቋማዊ ጥሰቶችንም መመርመር እንደሚያሻ፣ ካሣውንም ከተቋሞች ማግኝት እንደሚቻል የዘርፉ ባለሙያች ይመክራሉ። በገንዘብከሚተመኑ ካሣዎች ባሻገር የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባዎች የስነ-ልቦና እና የአካል ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላልና ተገቢውንሕክምና የሚያኙበት አጋጣሚ መመቻቸት ይኖርበታል። ጥሰቱም ዳግመኛ ላይደገም ለመቆሙ ማረጋገጫ ሊሰጥ፣ የተፈጠረውን በደልበአደባባይ መግለጽ፣ እንደተቋምም ይቅርታ ቢጠየቅ በተሻለ ወደ እርቅ ለመሸጋገር ይረዳል። የተፈጠረውን በደል በአደባባይበመግለጽ ብቻ ሳይሆን በስልጠና እና በትምህርት ስርዓት ውስጥ በማካተት ተገቢው እውቅና ሊሰጠውም ያሻል።የኮሚሲዮኑ መመስረቻ አዋጅ ስለ ካሳ የሚናገረው አንዳች ነገር የለም። ይሄም ቢሆን ኮሚሲዮኑ በምክረ-ሃሳቡ ላይ ተበዳዮችየሚካሱበትን አጋጣሚ ሊያካትት ይችላል።
ሰ. የተጠናቀረ ሪፖርት ከምክረ-ሀሳብ ጋር
የእውነት ሒደቱ ለእርቅ ቢያግዝም የመጨረሻው ሪፖርት ግን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለመፈጠሩ፣ አጠቃላይየሀገርን የፍትህ ስርዓት ክፍተቶችም እውቅና የሚሰጥ ወሳኝ አካሔድ ነው። ስለዚህ ኮሚሲዮኑ በአግባቡ የተጠናቀረ ሪፖርት ማቅረብይኖርበታል። ይሄ ሪፖርት ለምክር ቤት እንደቀረበም ወዲያውኑ በጽሑፍ መታተም ይኖርበታል። ሪፖርቱ መታተሙ እና ለሕዝብ ተደራሽመሆኑ ቆርሾ በተፈጠረባቸው መካከል የሚኖረው የእርቅ መንገድ ያፋጥነዋል። ሪፖርቱ የተፈጠሩትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ብቻሳይሆን፤ መሻሻል ስለሚገባቸው መንግስታዊ አሰራሮች፣ ተቋሞች እና የሕግ ማዕቀፎች ተገቢውን ምክረ-ሀሳብም ሊያካትት ይገባዋል።ይህ ምክረ-ሃሳብም በየጊዜው መቅረብ እና መንግስታዊ ተቋማትም አጽንሆት ሰጥተው መውሰድ፣ ለመፈጸምም በትጋት መስራትይጠበቅባቸዋል። እንደ ኮሚሲዮኑ መመስረቻ አዋጅ ኮሚሲዮኑ ...የሚደርስባቸውን መደምደሚያዎች እንደሁኔታው በየጊዜው ለሕዝብናለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት" የማሳወቅ ግዴታ ይጥለበታል። "በየጊዜው" የሚለው በምን ያህል ጊዜርቀት ውስጥ እንደሆነ ግን ግልጽ አይደለም። በዚህ ዙሪያ ምክረ-ሃሳቡን አስገዳጅ ማድረግ ሕገ መንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል ላይጥያቄ ሊያስነሳ ስለሚችል፣ ከአስገዳጅነት ይልቅ ተቋሞቹ በራሳቸው ፍቃድ አጽንኦት ሰጥተው እንዲወሰዱት ማመልከት ተመራጭ ይሆናል። አዋጁ የመንግስት ተቋማትየምክረ ሃሳቡ በቁም ነገር መውስድ እንደሚገባቸው የሚያትት ድንጋጌ ባይኖረውም፣ መንግስት ረጅም ጊዜና እና ወጪ የወጣበትንሒደት ወደ ጎን የሚተውበት አጋጣሚ ይኖራል ብሎ መገመት ግን አይቻልም።