ታህሣሥ 28 ፣ 2014

በባህርዳር ዲያስፖራዎችን ለመቀበል የተደረገ ዝግጅት

City: Bahir Darኢኮኖሚቱሪዝም ወቅታዊ ጉዳዮች

እንግዶች ወደ ባህር ዳር እንዲመጡ በተደጋጋሚ ጥሪያቸውን  አቅረበዋል።

Avatar: Abinet Bihonegn
አብነት ቢሆነኝ

አብነት ቢሆነኝ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ትምህርት ምሩቅ ሲሆን። ዜና እና የተለያዩ ዘገባዎች የመፃፍ ልምድ አለው። አሁን በአዲስ ዘይቤ የባህር ዳር ሪፖርተር ነው

በባህርዳር ዲያስፖራዎችን ለመቀበል  የተደረገ  ዝግጅት

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ.ር) የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡ የቱሪስት መስህቧ እና ተወዳጇ  ባህር ዳር ከተማም አንግዶችን ለመቀብል ተዘጋጅታለች።                                                                 

አዲስ ዘይቤ  ከከተማ አስተዳደሩ ባገኘችው መረጃ መሰረት  ከውጭ የሚመጡ እንግዶችን የሚመራ የዝግጅት ኮሜቴ ተዋቅሮ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችሉ የተለያዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች፣ ሁነቶች እና የውይይት መድረኮች   ተዘጋጅተዋል፡፡

ኢትዮጵያዊንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጥሪ ተከትሎ በከተማዋ የተደረጉ ዝግጅቶችን በተመለከተ የከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ መረጃዎች በማህበራዊ ገፃቸው ሲያጋሩ ሰንብተዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በሚዲያ የታቀዱ ሁነቶችን አና አጠቃላይ ዝግጅቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጠዋል፡፡ እንግዶች ወደ ባህር ዳር እንዲመጡ በተደጋጋሚ ጥሪያቸውን  አቅረበዋል።

መጭዎቹን ሀይማኖታዊ በዓላት እና ሀገራዊ ጥሪውንተከትሎ አንግዶች ወደ ባህር ዳር አንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚመጡትን ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለመቀብል  ዝግጀት አንደሚከተለው ቃኝተነዋል፡፡   

የእናት ሀገራቸውን  ጥሪ ተከትለው ሀገራቸው በምትፈልጋቸው ጊዜ ወደ ሀገራቸው የመጡ ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  በቆይታቸው አንዲደሰቱ ለማድረግ መታቀዱን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል ል፡፡ በዚህም አንደ ቤተሰብ ለመቀበል የሚያስችል የተለያዩ የኪነ ጥበብ ድግሶች ተዘጋጅተዋል፡፡  

እንግዶች በክልሉ ገናን በላሊበላ ጥምቀትን በጎንድር በድምቀት አንዲያከብሩ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በከተማዋ በሚኖራቸው ቆይታ ከተዘጋጁት የተለያዩ ዝግጅቶች በተጨማሪ የኢንቨስትመት አማራጮች መድረክ ተዘጋጅቶ፡  ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  ለመሳተፍ በዓሉ በኢንቨስትመንት አማራጮች እና ምቹ ሁኔታዎች አንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በዚህ ሀገራዊ ጥሪ ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ሁነቶች ያዘጋጀ ሲሆን ከነዚህም መካካል የፅዳት ዘመቻ፣የባህል ምግቦችና አልበሳት ኤግዚቪሽን፣ የገና ጨዋታ፣ የዘማች ቤተሰቦች ጥየቃ፣ የጎዳና ጉዞና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣የጀልባ ትሪትና የታንኳ ውድድር፣ የጎዳና ላይ ሩጫ ሌሎች ሁነቶች በከተማ አስተዳደሩ እና ሌሎች ተተባባሪ ድርጅቶች የታቀዱ ሁነቶች ተሰናድተዋል፡፡ 

"የጥኃት ብርሃን" የጀልባ ክራይ ማህበር ጣና ሀይቅን በጀልባ የሚያስጎበኙ አባላት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ሰላሳ ሰባት አባለት ያሉት ሲሆን የኮቪዲ ስርጭት እና ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ ምክንያት ስራቸው ተቀዝቅዞ አንደባጀ ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ይገልፃል፡፡አቶ ቻላቸው ጌትነት የማህበሩ ሊቀመንበር ሲሆን አሁን በሀገራችን የተዘጋጀውን የአንድ ሚሊየን ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጥሪ ለአንቅስቀሴውን ያነቃቃዋል የሚል ተስፋ አለው።

ሊቀመንበሩ "በቅድሚያ ሁሉንም አንደ ቤተሰብ እንኳን ደህና መጣችሁ ማለት እፈልጋለሁ" ይላል፡፡ "በከተማዋ ጊዜያቸውን ለማሳለፍ ለሚመጡ ወገኞቻችን ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት ተደርጓል" በዚህም ቴክኒካል ደህንነታቸው እና ፅዳታቸው የተጠበቁ ከስልሰ በላይ የጉብኝት ጀልባዎች መዘጋጀታቸውን የማህበሩ ፕሪዘዳንት አጫውተውናል፡፡

አንደሚታወቀው ባህር ዳር ከተማ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ያለበት ከተማ አደለችም፡፡ በአንፃሩ ሆቴል እና ሌሎች የአግልግሎት ዘርፎች በብዛት የሚስተዋሉባት ከተማ ናት፡፡ "ጃካራንዳ" ሆቴል ለከተማዋ ድምቀት ከሆኑ ባለ ኮከብ ሆቴሎች አንዱ ነው፡፡ አንደ ሌሎች ሆቴሎች ሁሉ የኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭት አና የሴሜኑ ጦርነት ለከተማዋ የንግድ አንቅስቃሴ ፈተና እንደነበር ይጋራሉ አቶ ደምሰው ሞሱ የሆቴሎ ስራ አስኬያጅ፡፡

ወደ ባህር ዳር የሚመጡ ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለመቀበል ሆቴሉ 10% ቅናሽ ማደረጉን ገልፀው ሆቴሉ በሚታወቅብት የስፖርት ባር ጨምሮ አጠቃላይ ዝግጅት ማድረጋቸውን ነግረውናል፡፡ አንግዶች በብዛት እንደሚመጡ ይጠበቃል ይላሉ፡፡

እንደ አቶ ደምሰው ገለፃ አጠቃለይ በከተመዋ ያለው ዝግጅት ጥሩ ነው ብለውነገር ግን ስጋታቸውን አልሸሸጉም  ከባህር ዳር ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ከተማ የፀጥታ ስጋት ያለበት አድርጎ የማሰብ እና ለጦርነቱ ቀጠና ቅርብ አድርጎ የመመልከት ጉዳይ በመኖሩ እንግዶች ምቾት እንዲሰማቸው የስዓት እላፊ ገደቡ ቢሻሻል  ይላሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በከተማ አልፎ አልፎ በባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች "ባጃጅ" የሚፈፀም  ወንጀል ሌሎች ስጋቶች  ሊታሰብበት ይገባል ይላሉ፡፡ 

ከተማዋ ከአሏት የቱሪስት መስህብ ቦታዎች መካከል 37 ገዳማት በላይ በውስጡ ያቀፈውን ታሪካዊ እና ጥንታዊ የጣና ገዳማት፣ ውብ የሆነውን የጣናን ሀይቅ፣ የዘጌ ገዳማት፣የተለያዩ የከተማዋ ውብ እና አስደናቂ መዝናኛዎች፣ የጢስ ዓባይ ፏፏቴ፣ በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት 17 ክፍለ ዘመን እንደተሰራ የሚነገርለት ጥንታዊው የአለት ድልድይ  እና ሌሎች የቱሪስት መስህብ ቦታዎች ይገኛሉ። "የዘንባባ ከተማ" በመባል በምትታወቀው ባህርዳር ከተማ ለእግር ጉዞ ምቹ የሆነች ከተማ እንደሆነች ይነገርላታል።

አስተያየት