ሰኔ 4 ፣ 2013

ፌስቡክ በኢትዮጵያ ለሚካሄድው ምርጫ ተዓማኒነት እየሰራሁ ነው አለ

ምርጫ 2013ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

ፌስቡክ የምርጫውን ተአማኒነት ለማረጋገጥ የሚሰራችው ስራዎች ላይ አዳዲስ የመቆጣጠሪያ መንገዶችን ይፋ ማድረጉን ዛሬ በምስራቅና አፍሪካ ቀንድ ቢሮዉ በኩል ባሰራጨው መግለጫ አስታዉቋል፡፡

ፌስቡክ በኢትዮጵያ ለሚካሄድው ምርጫ ተዓማኒነት እየሰራሁ ነው አለ

ፌስቡክ በኢትዮጵያ በሁለት ዙር ሰኔ 14ና ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሚካሄድው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተገናኘ የምርጫውን ተአማኒነት ለማረጋገጥ የሚሰራችው ስራዎች ላይ አዳዲስ የመቆጣጠሪያ መንገዶችን ይፋ ማድረጉን ዛሬ በምስራቅና አፍሪካ ቀንድ ቢሮዉ በኩል ባሰራጨው መግለጫ አስታዉቋል፡፡

ኩባንያው በሀገሪቱ በሚካሄደዉን ምርጫ በድምፅ አሰጣጡ ወቅትና ከዚያም በኋላ ሁከትን የሚቀሰቅሱ የጥላቻ ንግግሮችን እና ይዘቶችን ለመለየት እና ለማስወገድ ብሎም የተሳሳተ መረጃ ስርጭትን ለመቀነስ የሚያግዙ ተግባራትን አንደሚከውን አስታውቋል፡፡

ፌስቡክ በኢትዮጵያ የምርጫ ተአማኒነትን ለማገዝ ይረዳሉ በማለት ይፋ ካደረጋቸዉ ተግባራት መካከል የፌስቡክ የምርጫ ክወና ማዕከልን ስራ ማስጀመር አንዱ ሲሆን ይህም ምርጫዉ በሚከናወንበት ወቅት በማዕከሉ ባለሙያዎችን በመመደብ የምርጫዉ ሂደት ላይ አንቅፋት ይፈጥራሉ ተብለዉ የሚለዩ ይዘቶች ላይ ቁጥጥር በማድረግ አፋጣኝ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችል አሰራር አንደዘረጋ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ይህ አሰራር ሀገርኛ ዕውቀትንና መረዳትን እንደመጠየቁ የተሳሳቱ መረጃዎችን፣ የጥላቻ ንግግሮችን፣ የምርጫ መረጃዎችን የሚከታተሉ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉበት ቡድን ተዋቅሮ በስራ ላይ አንደሚገኙም ፌስቡክ ይፋ አድርጓል።

በተጨማሪም የጥላቻ ንግግርን እና ሌሎች ጎጂ ይዘቶችን ለማቆጣጠር ፌስቡክ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብትን የሚጥሱ ይዘቶችን ሲያዩ ሪፖርት እንዲያደርጉና ሪፖረት ማድረጊያ መንገዶችን በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ቀለል ያደረገ ሲሆን ይህም ፌስቡክን ለሚያከናውነው ምርመራ ያግዘዋል ሲል መግላጫዉ አስፍሯል፡፡

በምርጫ ወቅት፣ በፊትና በኋላ ሊታዩ የሚችሉ የጥላቻ ንግግሮችን ወይም አመፅን እና ብጥብጥን የያዙ ሊሆኑ ይችላል የሚላቸውን የይዘት እና አስተያየቶች ስርጭትን በእጅጉ ለመቀነስ ፌስቡክ ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ አንደሆነ የሚያስረዳዉ መግለጫዉ ባለሙያዎቹ ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ የፌስቡክ ፖሊሲዎችን እንደሚጥስ ካረጋገጡ ይዘቱ ወዲያዉኑ ከድረ ገጹ ላይ አንደሚወገድ ይገልጻል።

በተጨማሪም የተሳሳተ መረጃ እና የሐሰት ዜናዎችን ለመዋጋት፤ የተሳሳተ አድራሻ፣ ጊዜ ያለፈበት ወይም ዐውዱን ያልጠበቀ ምስል ችግሮችን ስለመፍታት፤ የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ግልጽነት ለማሻሻል የሚረዱ ተግባራትን ጭምር እየከወነ አንደሚገኝም ይፋ አድርጓል፡፡

ከመጋቢት 2020 እስከ መጋቢት 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ ፌስቡክ በኢትዮጵያ ውስጥ 87,000 የጥላቻ ንግግሮችን አስወግዷል፣ ከእነዚህ ውስጥ 89% የሚሆኑት በተጠቃሚዎች ሪፖረት ከመደረጋቸው በፊት ተገኝተው እርምጃ አንደተወሰደባቸዉም መግለጫዉ አስታውሷል፡፡

አስተያየት