ታህሣሥ 13 ፣ 2013

ጅማ፡ “አርሶ-አደሮች ማሽኖችን በሚገባ እየተጠቀሙ አይደለም፡፡” 

City: Jimmaንግድምጣኔ ሀብት

በኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የጅማ ግብርና ምህንድስና ማዕከል የሚሰሩ የግብርና ቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑት ማሽኖች በተገቢው መንገድ ወደ ህብረተሰቡ እየወረዱ አለመሆኑ ተገለፀ፡፡

Avatar: Workineh Diribsa
Workineh Diribsa

I am Workineh, lecturer and researcher at Jimma University; journalist/correspondent for Addis Zeybe media.

ጅማ፡ “አርሶ-አደሮች ማሽኖችን በሚገባ እየተጠቀሙ አይደለም፡፡” 

በኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የጅማ ግብርና ምህንድስና ማዕከል የሚሰሩ የግብርና ቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑት ማሽኖች በተገቢው መንገድ ወደ ህብረተሰቡ እየወረዱ አለመሆኑ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው በትላንትናው ዕለት ታህሳስ 12፣ 2013 ዓ.ም በጅማ ከተማ በተዘጋጀ የግብርና ቴክኖሎጂ ማሽኖች አውደ ርዕይ ሲሆን 43 የግል እና የመንግስት ተቋማት ተሳትፈውበታል፡፡  

በማዕከሉ የግብርናና ግብርና ማሽነሪ ተመራማሪ የሆነው አቶ ጥበቡ አበቡ  “የህብረተሰቡ ቴክኖሎጂን የመቀበል ንቃተ-ህሊናና የኢኮኖሚ አቅሙ ደካማ መሆን ለችግሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላው” ይላል፡፡ ዋጋቸው ከአንድ ማሽን ወደ ሌላ የሚለያይ ሲሆን እንደ አነስተኛ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን ያሉት በአማካይ እስከ 30ሺህ ብር የቡና መፈልፈያ ማሽኖች ደግሞ 10ሺህ ብር የሚያወጡ ናቸው፡፡

በማዕከሉ የግብርና መካናይዜሽን ተመራማሪ  የሆነው ዋሲሁን ምትኩ  በበኩሉ በገበሬው በኩል ከሚታይ የበጀት ማነስ ይልቅ ደግሞ ጎልቶ ስለሚስተዋለው ቴክኖሎጂ የመጠቀም ስጋት ሲገልጽ “አንዳንዴ በጥቃቅንና አነስተኛ ተሰርቶ ለገበሬው የሚቀርቡ አንዳንድ የግብርና ማሽኖች በተለያዩ ምክንያቶች ጥራታቸውን ያልጠበቁ ከሆኑ ገበሬው ከዛ በኋለ ሁሉም ማሽን እንደዛው ችግር ያለው ይመስለዋል፡፡ ለምሳሌ የኛ ግብርና ምህንድስና ማዕከል ለጅማ፣ ቡኖ በደሌና ኢሉ አባቦር ዞኖች ሀላፊነት ቢኖርበትም በተጠቀሱት ምክንያቶች ብዙን ጊዜ ኢሉአባቦር ዞን መድረስ አልቻልንም » ይላል

ለእይታ ከቀረቡት የግብርና ቴክኖሎጂ ውጤቶችም ቡና መፈልፈያ፣ ቡና ማጠቢያ፣ ኦቾሎኒ መፈልፈያ፣ የመስኖ መሳብ፣ የሰም ማቅለጫ፣ የከብቶች ምግብ መቁረጫ፣ የቦቆሎ መፈልፈያ ማሽኖች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ (ወርቅነህ ድሪብሳ)

አስተያየት