ነሐሴ 4 ፣ 2010

አስፈላጊ ጸብ ከራስ ማህበረሰብ መፈክር ጋር

ፖለቲካSocietyምጣኔ ሀብት

በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ጸብ የሚለው ቃል ገንቢ ክርክር፡ ምክክር፡ ምርምር፡ ጥያቄን የሚወክል ነው፡፡ለመጪዋ ኢትዮጵያ ዓላማችንና ህልማችን ምንድነው?እኔ ‹የመላው…

አስፈላጊ ጸብ ከራስ ማህበረሰብ መፈክር ጋር
በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ጸብ የሚለው ቃል ገንቢ ክርክር፡ ምክክር፡ ምርምር፡ ጥያቄን የሚወክል ነው፡፡ለመጪዋ ኢትዮጵያ ዓላማችንና ህልማችን ምንድነው?እኔ ‹የመላው ዜጎቿን ሰብዓዊ መብት፡ ሉዓላዊነትና ክብር የምትጠብቅና የበለጸገች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መፍጠር ነው› ብዬ አምናለሁ፡፡ከብዙ ዘመናት የዜጎች መስዋዕትነት በኋላ ወደ ዲሞክራሲያዊ ምርጫና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚወስደን ሁኔታ ፍንጩ ገና በታየበት በአሁኑ ወቅት ከሰከነ ውይይት ይልቅ ያደሩ አደንቋሪ መፈክሮችና አላስፈላጊ አተካሮዎች በየጊዜው እየተነሱ አየሩን ይቆጣጠሩታል ፡፡‹‹ጭቆናን የተሸከመ ህዝብ ዴሞክራሲን መሸከም ያቅተው ይሆን?›› እስኪባል ድረስ፡፡ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሊገነባ የሚችለው ምርጫን በጸጋ ሊቀበል በሚችል ህብረተሰብ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የሚገነባው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውጤታማ እንዲሆን መጀመሪያ ቢያንስ ከየማህበረሰቡ በመሰረታዊ አገራዊ ማንነቶችና ትርክቶች ላይ ከሌሎች ማህበረሰቦች ጋር ስምምነት ያለው ህብረተሰብ ሊኖር ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ በሌለበት ሁኔታ የሚካሄደው ምርጫ የቱንም ያህል ዴሞክራሲያዊ ነው ቢባልም ከአገር አመራር እና አስተዳደር ርዕዮተ- ዓለም ባለፈ የማህበረሰቦችን ማንነትና እጣ ፈንታ የሚወስን፡ ለአንዱ ኩራት ለሌላው ፈጽሞ ውርደት የሆኑ አስተሳሰቦች ለምርጫ ቀርበው የሚመጣን የምርጫ ውጤት ‹በጸጋ መቀበል› የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ይህንን መግባባት ለመፍጠር አስፈላጊ የሆነው የሰከነ ውይይት ግን ከየማህበረሰቡ በወል በሚስተጋቡ መፈክሮች በተወጠረ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ሊከናወን ይችላል?****************************************************በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥነው ጽሑፍ እዚህ ያገኙታል፡፡ ዘለግ ያለ ትንታኔ ያለው ስለሆነ ከጸሐፊው ጋር በመነጋገር ወደ ኮምፕዩተርዎ ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክዎ አውርደው እንዲያነቡት ወደድን፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የቀረቡት ሐሳቦች የጽሐፊውን አመለካከት የሚውክሉ ናቸው፡፡

አስተያየት