የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ከማስተር ፕላን ትግበራ ቁጥጥር ጋር በ17 ቦታዎች ባካሄደው የናሙና ጥናት ዘጠኙ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውሉ ስምንቱ ከታለመላቸው አገልግሎት ውጭ ውለው መገኘታቸው ታውቋል።
የተለመደ የቀድሞ ሥራቸውን በአዲስ አመራር የቀጠሉት ከአንድ ሺህ በላይ የፋብሪካው ሰራተኞች ከአዲሱ አመራር ጋር አለመግባባት ውስጥ እንደሚገኙ ስማችን እንዳይጠቀስ ያሉ የፋብሪካው ሰራተኞች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።
መረጃው በግል ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች በመንግስት ተቋማት እየተማሩ ከሚገኙት ጋር ሲነጻጸር በ2ሺህ 400 ተማሪዎች ብልጫ አለው። በትምህርት ቤቶች ብዛትም የግል ተቋማት ከመንግሥታዊዎቹ በ5 እጥፍ ይበልጣሉ።
በቀን 13,322 አምርታ ለነዋሪዎቿ ማከፋፈል ብትችልም ከፍላጎቱ አንጻር ማዳረስ የቻለችው 22 በመቶውን ብቻ ነው።
የፍጥነት መገደቢያዎቹ በርከት ያለ ቁጥር ያለው ህዝብ ያለበት ቦታ ስለሚገኙ በአግባቡ መገንባታቸው የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው
መናኸሪያው የራሱ አጥር የሌለው በመሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ነው።
በሰዓቱ ማጠር ምክንያት ጥቂት የማይባሉ ተጓዦች የሚጓዙበት አውቶብስ ጥሏቸው በመሄዱ ለእንግልት እዳረጉ ነው።
“ብርሃን ለሁሉ” እ.ኤ.አ 2017 ዓ.ም. የተጀመረው የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን መርሃ-ግብር ሁለተኛ ምዕራፍ ነው።
ከወንጂ ማዞሪያ ወደ ሥላሴ በሚወስደው የአስፖልት መንገድ ላይ ከአዳማ ትራክተር መገጣጠሚያ ፊት ለፊት የሚገኘው አካባቢ እጅግ ውብና አረንጓዴ ገጽታን የተላበሰ ነው።
አሰልቺውን ሰልፍ፣ ለቀናት የተራዘመውን ጥበቃ እንደሚያቃልል የታመነበት አገልግሎት የታለመለትን ዓላማ እንዳልመታ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ይናገራሉ።