የካቲት 15 ፣ 2013

“ለሁለቱም ፅንፈኛ ኃይሎች ግልፅ መልዕክት እናስተላልፋለን” አቶ ሽመልስ አብዲሳ

City: Addis Ababaዜናዎች

ከደቡብ ክልል ልዩ ዞንነት ወደ ክልልነት ለማደግ የሚያበቃዉን ይሁንታ ያገኘዉ የሲዳማ ክልል 10ኛዉ የኢትዮጵያ ክልል በመሆን በሐዋሳ ከተማ ይፋዊ የመንግስት ምስረታ አካሄዷል።

“ለሁለቱም ፅንፈኛ ኃይሎች ግልፅ መልዕክት እናስተላልፋለን” አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ከደቡብ ክልል ልዩ ዞንነት ወደ ክልልነት ለማደግ የሚያበቃዉን ይሁንታ ያገኘዉ የሲዳማ ክልል 10ኛዉ የኢትዮጵያ ክልል በመሆን በሐዋሳ ከተማ ይፋዊ የመንግስት ምስረታ አካሄዷል።

በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባስተላለፉት መልዕክት “ዛሬ ከሐዋሳ ከተማ ለሁለቱም ፅንፈኛ ኃይሎች ግልፅ መልዕክት እናስተላልፋለን” ማለታቸው ተደምጧል።

“ብልፅግና ፀረ-አንድነትም አህዳዊም አይደለም” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ “የመሃሉን መንገድ ይዘን እንቀጥላለን” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ መልዕክት እናስተላልፍላቸዋለን ያሏቸውን ሁለት ፅንፈኛ ኃይሎች ግን በስም ከመጥራት ተቆጥበዋል። 

 አቶ ሽመልስ “የሲዳማ ወጣት ላለፉት ብዙ አስርት ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል እንዳደረገ ጠቅሰው የትግሉ ሰማዕታት ዛሬ ከሰማይ ሆነው ወደታች የሲዳማ ክልል መመስረቱን ሲያዩ እንዴት ደስ እንደሚላቸውና እንደሚያርፉ ምንም ጥርጥር የለውም” ብለዋል።

“አንዳንዶች በፌስቡክ እና ዩቱብ ጫጫታ ኢትዮጵያ የምትፈርስ ይመስላቸዋል” ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ “ኢትዮጵያ ግን አፍራሾቿን ሁሉ እያፈረሰች አንድነቷን ጠብቃ ትቀጥላለች” ሲሉ ገልፀዋል።

“ኢትዮጵያን አፍኜ እይዛለሁ የሚል ኃይል በሙሉ በኢትጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ይሸነፋል” ሲሉ የተደመጡት አቶ ሽመልስ “ለአዲሱ ሙሽራ ክልል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 100 ሚሊዮን ብር መድቧል” ሲሉ አስታውቀዋል።

በዝግጅቱ ላይ “አለቃዬ ክቡር ፕሬዝደንት አቶ ደስታ ሌዳሞ” እያሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ሲገልፁ የነበሩት አቶ ሽመልስ “ፍቼ ጫምባላላን ክልል መስርተን እናከብራለን እንዳልነው አሁን ደግሞ ቀጣዩን ምርጫ አሸንፈን ፍቼ ጫምባላላን በልዩ ሁኔታ በኦሮሚያና በሲዳማ በአንድነት እናከብራለን” ብለዋል።

 

አስተያየት