ሰኔ 11 ፣ 2013

የአዋሽ ባንክ የደንበኖች ተቀማጭ ሂሳብ 100 ቢሊየን ብር ደረሰ

ንግድ

አዋሽ ባንክ በባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 100 ቢሊየን ብር መድረሱን ባንኩ አስታዉቋል፡፡ ይህም ባንኩን በኢትዮጲያ የመጀመሪያዉ የግል ባንክ አንደሚያደርገዉ ታዉቋል፡፡

Avatar: Solomon Yimer
ሰለሞን ይመር

Solomon is a content editor at Addis Zeybe. He has worked in print and web journalism for six years.

የአዋሽ ባንክ የደንበኖች ተቀማጭ ሂሳብ 100 ቢሊየን ብር ደረሰ

አዋሽ ባንክ በባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 100 ቢሊየን ብር መድረሱን ባንኩ አስታዉቋል፡፡ ይህም ባንኩን በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የግል ባንክ አንደሚያደርገዉ ታዉቋል፡፡

ባንኩ በዛሬዉ አለት ይህንን አስመልክቶ ባስተላለፈዉ መልዕክት “ይህ ውጤት የተገኘው ክቡራን ደንበኞቻችን በባንካችን ላይ ባላችሁ እምነት እና ከኛ ጋር ስለሰራችሁ ስለሆነ በዚሁ አጋጣሚ ለውድ ደንበኞቻችን የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን ለወደፊቱም በበለጠ ደረጃ ልናገለግላችሁ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን” ብሏል፡፡

ባለፈዉ አመት የአዋሽ ባንክ ከደንበኞቹ መሰብሰብ የቻለዉ 70.6 ቢሊየን ብር ነበር ይህም ማለት ባንኩ በዚህ አመት ተጨማሪ 30 ቢሊየን ተቀማጭ ብር ከደንበኞቹ ለመሰብሰብ ችሏል ማለት ነዉ፡፡

ባንኩ ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም.ባወጣዉ መረጃ መሰረት የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠኑን ከ120 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ መቻሉንና የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑንም ወደ 91.2 ቢሊዮን ብር ማሳደጉን ገልጾ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህም በኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛውን የሀብት መጠን የያዘ የግል ባንክ አድርጎታል፡፡ እስካሁን አጠቃላይ የሀብት መጠኑን ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ የግል ባንክ የለም፡፡

በሌላ በኩል ከባንኩ የተገኘዉ መረጃ አንደሚያሳየዉ  ከሆነ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 8.1 ቢሊየን መድረሱንና ይህም በኢትዮጵያ ካሉ ባንኮች ቀዳሚዉ አንዲሆን ያስችለዋል፡፡በተጨማሪም አዋሽ ባንክ ለደንበኞቹ የሰጠው የብድር መጠን 81.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ 

ከተመሰረተ 25 ዓመታት ያለፉት አዋሽ ባንክ በአሁኑ ሰዓት  በመላዉ ሀገሪቱ 540 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ፡፡ የሠራተኞቹን ቁጥር ደግሞ ከ11,758 በላይ ማድረስ ችሏል፡፡

አስተያየት