መስከረም 6 ፣ 2013

የአውሮፓ ህብረት በአንበጣ ወረርሺኝ ለተጠቁ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ አደረገ

ዜናዎች

የአውሮፓ ህብረት በአፋር፣ አማራ፣ ሶማልያ፣ ኦሮምያና ትግራይ ክልሎች ለሚገኙ በአንበጣ ወረርሺኝ ለተጠቁ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ የሚውል የ86.8 ሚልዮን ብር…

የአውሮፓ ህብረት በአንበጣ ወረርሺኝ ለተጠቁ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ አደረገ
የአውሮፓ ህብረት በአፋር፣ አማራ፣ ሶማልያ፣ ኦሮምያና ትግራይ ክልሎች ለሚገኙ በአንበጣ ወረርሺኝ ለተጠቁ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ የሚውል የ86.8 ሚልዮን ብር (2 ሚልዮን ዪሮ) ድጋፍ ለተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ማድረጉን ሪሊፍ ዌብ ዘገበ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመረጃ መካነድር የሆነው ሪሊፍ ዌብ እንደዘገበው ከሆነ ከዚህ ቀደም በግንቦት ወር ካደረገው የ104.2 ሚልዮን ብር (2.4 ሚልዮን ዪሮ) በመቀጠል በህብረቱ የተደረገ ድጋፍ ነው። እንደዘገባው ከሆነ በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝና በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አማካኝነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህፃናት መርጃ ድርጅት ለመርዳት አቅዶ ከነበረው ቁጥር በ24% ጭማሬ ታይቷል። ይህም ከዚህ ቀደም ስደተኞችን ጨምሮ በፈረንጆቹ አመት መጀመርያ ተገምቶ የነበረው ቁጥር 460,000 ሲሆን በአሁኑ ወቅት ይህ ቁጥር ስደተኞችን ጨምሮ 570,000 ደርሷል።በተጨማሪም ከዘገባው መረዳት እንደሚቻለው ከሆነ በተሰጠው ድጋፍ አማካኝነት የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ለ60,000 ያህል በምግብ እጥረት የተጎዱ ህፃናትና ለ3,000 በስታብላይዜሽን ማዕከላት የሚገኙ ህፃናትን የሚንከባከቡ ግለሰቦች የምግብ አቅርቦት ያደርጋል። በወቅቱ በአገሪቱ የሚገኘው የበረሃ አንበጣ ወረራ በ25 አመታት ያልታየ ሲሆን ከኮሮና ወረርሺኝ አሉታዊ ተፅዕኖ ጋር ተደምሮ በአማራ፣ ኦሮምያ፣ ትራይ፣ ሶማልያና አፋር ክልሎች ላይ የምግብ ዋስትና ችግርን እየፈጠረ እንደሚገኝ ከዘገባው መረዳት ይቻላል። በተጠቀሰው የአንበጣ ወረራ አማካኝነት እንደየተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ከሆነ በመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም 126,000 ህፃናትን ጨምሮ አንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን የምግብ እርዳታ ሊያሻቸው ይችላል። 

አስተያየት