መስከረም 6 ፣ 2013

በኢትዮጵያ የመጀመርያው በባቡር ሀዲድ የተደረገው የአትክልት ኤክስፖርት

ዜናዎች

ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ገበያ የምታቀርበውን የአቮካዶ ምርት ለመጀመርያ ጊዜ በባቡር ከሞጆ ደረቅ ወደብ እስከ ጅቡቲ ወደብ ማጓጓዟን ሬልዌይ ጋዜት ኢንተርናሽናል…

በኢትዮጵያ የመጀመርያው በባቡር ሀዲድ የተደረገው የአትክልት ኤክስፖርት
ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ገበያ የምታቀርበውን የአቮካዶ ምርት ለመጀመርያ ጊዜ በባቡር ከሞጆ ደረቅ ወደብ እስከ ጅቡቲ ወደብ ማጓጓዟን ሬልዌይ ጋዜት ኢንተርናሽናል (Railway Gazzette International) ዘገበ። መካነ ድሩ በዛሬው እለት ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ናሽናል ኩል ሎጂስቲክስ ኔትወርክ (Naitional Cool Logistics Network) በተሰኘው ድርጅት የተደረገው የመጀመርያ የባቡር ጉዞ 24 ቶን አቮካዶ አቀዝቅዞ ወደ ወደቡ በማድረስ በአይነቱ የመጀመርያ እንደሆነ ዘገባው ያስረዳል።ርቀቱ 750 ኪ.ሜ ያህል የሚሆነው የባቡር ጉዞ ወደ ጅቡቲ ወደብ የተጠቀሰውን የአቮካዶ ኤክስፖርት ካደረሰ በኋላ በባህር ጉዞ ወደተለያዩ የአውሮፓ አገራት ምርቱ እንደሚዳረስ ዘገባው ያስረዳ ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ በቀጣይ የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀምን ከመጨመር በተጓዳኝ የአትክልትና ፍራፍሬ ኤክስፖርትን እንደሚደግፍ የጂቡቲ ወደብ ባለስልጣን ሀላፊ አቡበከር ኦማር ሃዲ ተናግረዋል።ናሽናል ኩል ሎጂስቲክስ ኔትወርክ የተሰኘው ድርጅት በቀጣይ በአዲስ አበባ ዙርያ እየገነባ የሚገኘው ኩል ፖርት አዲስ (Cool Port Addis) የተሰኘውን የምርት ማከማቻ ገንብቶ በሚጨርስበት ወቅት ለአገሪቱ የአትክልትና ፍራፍሬ ፍጆታ እንዲሁም ኤክስፖርት ትልቅ አስተዋፆ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ ለአገራዊ፣ አህጉራዊና አለምአቀፍ ገበያ የሚቀርበው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትን በማጓጓዝ ትልቅ ሚናን ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

አስተያየት