You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
ሜጋዶ ጎልድ (Megado Gold IPO) የተሰኘው ድርጅት በታሪካዊዋ የኢትዮጵያ ገዢ ንግስት ሳባ ግዛት ላይ የሚደረገውን የወርቅ ፍለጋ ፋይናንስ እንደሚያደርግ ስሞል ካፕስ (Small Caps) የተሰኘው መካነድር ዘገበ። የንግስት ሳባ ግዛት በአሁኑ ወቅት ቢለካ ከኢትዮጵያ እስከየመን ድረስ እንደሚዘልቅ ያስታወሰው ዘገባው ድርጅቱ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት 25 ሚልዮን ሼሮችን በመሸጥ እስከ 182,500,000 ብር (5 ሚልዮን ዶላር) ድረስ ለፕሮጀክቱ ለመሰብሰብ እንዳቀደ ዘገባው ያስረዳል።በወቅቱ ሜጋዶ ስድስት የተለያዩ የማዕድን ፈቃዶችንንና አንድ በመፅደቁ ሂደት ላይ የሚገኝ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ ያለው ሲሆን በወቅቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የማዕድን ማውጣት ስራን በመስራት ላይ ይገኛል። በርከት ያለ የወርቅ ክምችት እንዳለው የሚነገርለትን የዲሽ ተራራን ጨምሮ ለጋ ደምቢ፣ ሳካሮና ቱሉ ቄፒ በተሰኙት ቦታዎች ላይ በርከት ያለ የወርቅ ክምችት እንዳለ ከዘገባው መረዳት ይቻላል። መቀመጫውን በአውስትራሊያ ያደረገው ማጋዶ ጎልድ በአውስትራልያን ሴኪውሪቲስ ኤክስቼንጅ (Australian Securities Exchange) ላይ የሚጫረት ድርጅት ሲሆን የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚካኤል ገምብሌይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ላለፉት 15 አመታት ያህል እንደሰራ ከዘገባው መረዳት ይቻላል። በተጨማሪም ሚካኤል በኢትዮጵያ እስከ 2.9 ቢልዮን ብር እንዲሁም በአፍሪካ ደግሞ እስከ 18.2 ቢልዮን ብር ድረስ የሚገመቱ ፕሮጀክቶችን ማስተዳደሩ ለተጠቀሰው የወርቅ ፍለጋ ፕሮጀክት ስኬት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በመረጃው ተቀምጧል።