ለቀደምቷ የምስራቅ ፈርጥ ድሬዳዋ ከተማ ድምቀት የሆኑት የከዚራ ዛፎች በተለይም የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ሀዲድ ዝርጋታን ተከትሎ የፈረንሳይ ዜጎች ችግኞቹን መትከል እንደጀመሩ መረጃዎች ያመለክታሉ ፡፡
በከተማው ያልተመዘገቡና ህጋዊ ፍቃድ የሌላቸው ተሽከርካሪዎችን ተጠቅመው ግድያ፣ ዝርፊያና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ሰርተው ሚሰወሩም አሸከርካሪዎችን ለመቆጣጠር” አገልግሎት ሰጭዎች የደንብ ልብስ አንዲለብሱ መመሪያው ያስገድዳል።
በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በጎንደር ከተማ በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ተገንብቶ የካቲት 15/2015 ዓ.ም የተመረቀው የዳቦ ፋብሪካው ስራ አለመጀመሩ ተሰምቷል ፡፡
ህዝቡ በተጀመረው የትራንስርት አገልግሎት በዘላቂነት ተጠቃሚ መሆን እንዲችል የተጀመረው የነዳጅ አቅርቦት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በትግራይ የትራንስርት አገልግሎት ሰጭዎች ጠየቁ ።
ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ ድርቅ በተከሰተባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከ6 ሚሊየን በላይ እንስሳት ሲሞቱ 11 ሚልየን ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን አጥተዋል
ሴትን ልጅ ለአቅመ ሔዋን ሳትደርስ ትዳር እንድትመሰርት በሚደረግበት የጎንደር እና አካባቢው ማህበረሰብ መንግስት ያለ እድሜ ጋብቻን ለማስቀረት ለሚደረገው ጥረት ፈተና እንደሆነበት ይገልፃል
የውሃ መያዣ ፕላስቲኩን ሰማያዊ ቀለም የሚሰጠው ጥሬ እቃ መቅረቱ በዓመት 50 ሚልየን ዶላር እንዲቆጠብ ቢያደርግም ለዋጋው መናር ፋብሪካዎች የችርቻሮ ነጋዴዎችን ይወቅሳሉ
“ለእኔ ትምህርት ይጀመራል የሚል ዜና ከመስማት ሌላ የሚያስደስተኝ ነገር የለም” የሚሉት ተማሪዎች በፍጥነት ትምህርት የሚጀመርበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል
በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ አህያዎች በኢትዮጵያ እንደሚታረዱ የተገለፀ ሲሆን በዚህ ከቀጠለ ሀገሪቱን አህያ ከማሳጣት ባለፈ የስራ ጫናዎችን በመፍጠር ማህበራዊ ቀውስም ሊያስከትል ይችላል
“በሃገራችን ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሃብቶችን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ባለመደረጋቸው ከአካል ጉዳተኞች መገኘት ያለበትን ገቢ እንዲያገኝ የሚያስችል ደረጃ ላይ አልተደረሰም”